በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክል ኮኽን ወደ ወህኒ ቤት ተላኩ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የቀድሞ የግል ጠበቃ ማይክል ኮኽን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የቀድሞ የግል ጠበቃ ማይክል ኮኽን

ከየዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የቀድሞ የግል ጠበቃ ማይክል ኮኽን ፕሬዚዳንቱ ጋር በድብቅ ወሲባዊ ግንኙነት ነበራቸው ለተባሉ ሁለት ሴቶች አፍ ማዘጊያ ገንዘብ በመክፈልና በሌሎች ወንጀሎች የቀረቡባቸው ክሶች ተረጋግጠውባቸው ትላንት ወደ ወህኒ ቤት ተልከዋል።

ሕግ ጥሼ የተገኘሁት ከፕሬዚዳንት ትራምፕ በተሰጠኝ ትዕዛዝ መሠረት ነው ሲሉ የዕምነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ማይክል ኮኽን ትላንት ከኒውዮርክ አፓርተማቸው ተይዘው ወደ ፌዴራሉ እሥር ቤት ሲወሰዱም ገና ብዙ የማጋልጠው ሚሥጥር አለ ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ሌሎች በርካታ የሪፖብሊካን ፓርቲው አመራሮች ማይክል ኮኽን ይዋሻል ሲሉ ለማደናቀፍ ሞክረዋል።

አምስት የፕሬዚዳንቱ የቀድሞ ረዳቶች በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በእሥር ላይ ይገኛሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG