በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባስራ ውስጥ በተፈጠረ መረጋገጥ አንድ ሰው ሲሞት ብዙዎች ቆሰሉ


የኢራቅ ደጋፊዎች በደቡባዊ ኢራቅ ከተማ የደጋፊዎች ዞን በሚል በተሰየመ ሥፍራ የእግር ኳስ ጨዋታ ሲመለከቱ
የኢራቅ ደጋፊዎች በደቡባዊ ኢራቅ ከተማ የደጋፊዎች ዞን በሚል በተሰየመ ሥፍራ የእግር ኳስ ጨዋታ ሲመለከቱ

በደቡባዊቱ የኢራቅ ከተማ ባስራ ውስጥ ስቴዲየም ደጃፍ ላይ በተፈጠረ ግፊያና መረጋገጥ አንድ ሰው ሲሞት ሌሎች ብዙ ሰዎች መቁሰላቸውን የሀኪም ቤትና የፀጥታ ምንጮች አስታወቁ።

አደጋው የደረሰበት ትርምስ የተፈጠረው የፋርስ ባህረ ሰላጤ ሀገሮች የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ በሚካሄደበት ስታዲየም ደጅ ላይ ነው።

ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ግጥሚያዎችን እንዳታስተናግድ ለረጅም ጊዜ ታግዳ የቆየችው ኢራቅ ገፅታዋን ለማደስ እየጣረች ሲሆን ቀደም ሲል ለነበሩ የዝግጅት አደረጃጀት ግድፈቶችም ይቅርታ ጠይቃለች።

በኢራቅና በኦማን መካከል በአዲስ አበባ ጊዜ ዛሬ ተስያት አሥር ሰዓት ላይ በሃገሬው ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ የተጀመረውን ግጥሚያ ለመመልከት በሺሆች የተቆጠሩ ቲኬት የሌላቸው ስታዲየሙ ፊት ለፊት ከሌሊት ጀምረው ተሰብስበው እንደነበር ታውቋል።

XS
SM
MD
LG