በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማንሃይም በተባለች የጀርመን ከተማ አንድ መኪና የተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በመውጣቱ አንድ ሰው ሞተ


በጀርመን ማንሃይም ከተማ  ውስጥ አንድ መኪና በዓል ለማክበር ወደተሰበሰበው ሕዝብ ጥሶ ገብቶ ጥቃት ካደረሰ በኋላ የአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች በቦታው አጠገብ ቆመው ይታያሉ፣ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም.
በጀርመን ማንሃይም ከተማ  ውስጥ አንድ መኪና በዓል ለማክበር ወደተሰበሰበው ሕዝብ ጥሶ ገብቶ ጥቃት ካደረሰ በኋላ የአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች በቦታው አጠገብ ቆመው ይታያሉ፣ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም.

በምዕራባዊ ጀርመን ማንሃይም ከተማ ውስጥ አንድ መኪና በዓል ለማክበር ወደተሰበሰበው ሕዝብ ጥሶ ገብቶ ባደረሰው ጥቃት አንድ ሰው ሲሞት በርካቶች መቁሰላቸውን የፖሊስ ቃል አቀባይ ዛሬ ሰኞ አስታወቁ።

ቃል አቀባዩ ፣የመኪናው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸው ፣ በድርጊቱ ላይ የተሳተፉ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ስለመኖር አለመኖራቸው የታወቀ ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል።

ፖሊስ ሰዎች ከስፍራው እንዲርቁ ጠይቋል። ክስተቱ የፈጠረው በምዕራብ ጀርመን ራይንላንድ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች የአደባባይ ከብረበዓል ለማክበር ሰልፍ በመውጡበት እና ሕዝብ በተሰበሰበበት ወቅት ነው።

ፓራዴፕላትዝ ከተሰኘው የከተማው መሀል አደባባይ ተነስተው፣ ፏፏቴ ወደሚገኝበት ቦታ በመጓዝ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ፣ አንድ ጥቁር ኤስ.ዩ.ቪ ተሽከርካሪ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ሰዎች ላይ እያበረረ መንዳቱን የሀገር ውስጥ ብዙኅን መገናኛ ዘግበዋል።

በጀርመን በዚህ ዓመት በታኅሣሥ ወር በማግደበርግ እና በሙኒክ የመኪና ግጭት የተገደሉትን ጨምሮ፣ የቦንብ ጥቃቶች እንዲሁም በጎርጎሮሳውያኑ ግንቦት 2024 በማንሃይም በጩቤ የተገደለውን ጨምሮ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ተከታታይ የኃይል ጥቃቶችን መፈጸማቸውን ተከትሎ በጀርመን የደኅንነት ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል።

እስላማዊ መንግሥት ተብሎ ከሚታወቀው ታጣቂ የሽብር ቡድን ጋራ ግንኙነት ያላቸው የማኅበራዊ መገናኛ፣ በኮሎኝ እና ኑረምበርግ በተደረጉት ዝግጅቶች ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር ከጠየቁ በኋላ፤ ፖሊስ ለዘንድሮው የጎዳና ዐውደ-ትሪዒት በተጠንቀቅ ላይ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG