በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጀርመን አየር ማረፊያዎች የተካሄደው የአንድ ቀን የሥራ ማቆም አድማ በረራዎችን አስተጓጎለ


ዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ዋና ዋና ማዕከሎችን ጨምሮ በ13 የጀርመን አየር ማረፊያዎች የተካሄደው የአንድ ቀን የሥራ ማቆም አድማ ጉዟቸውን ያስተጓጎላቸው መንገደኞች ሻንጣ
ዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ዋና ዋና ማዕከሎችን ጨምሮ በ13 የጀርመን አየር ማረፊያዎች የተካሄደው የአንድ ቀን የሥራ ማቆም አድማ ጉዟቸውን ያስተጓጎላቸው መንገደኞች ሻንጣ

የፍራንክፈርት እና የሙኒኩን ጨምሮ በ13 የጀርመን አውሮፕላን ጣቢያዎች እና ሌሎች የሀገሪቱ ዋና መዳረሻዎች፤ ሠራተኞች በዛሬው ዕለት ያደረጉት የአንድ ቀን የሥራ ማቆም አድማ ቀደም ሲል ጊዜ ተይዞላቸው የነበሩ አብዛኛዎቹ በረራዎች እንዲሰረዙ ምክኒያት ሆኗል።

ትላንት እሑድ እኩለ ለሊት ላይ የጀመረው እና ለ24 ሰዓታት እንዲቀጥል የታቀደው የሥራ ማቆም አድማ፤ በአውሮፕላን ጣቢያዎቹ የሚያገለግሉ ከአየር ማረፊያ ጋራ የተዛመዱ የምድር አገልግሎቶች ሥራ የሚሠሩ እና የደኅንነት ሠራተኞችን ያካተተ ነው።

በፍራንክፈርት አውሮፕላን ጣቢያ ለዕለቱ ታቅደው ከነበሩት ቁጥራቸው 1 ሺሕ 54 ከሚደርሱት በረራዎች 1 ሽሕ 116ቱ መሰረዛቸውን የጀርመን ዜና አገልግሎት የሀገሪቱን የአየር ትራፊክ አስተዳደር ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከበርሊን አውሮፕላን ጣቢያ የሚነሱ እና የሚመለሱ መደበኛ በረራዎች በሙሉ የተሰረዙ ሲኾን፤ ከሃምቡርግ አውሮፕላን ጣቢያ የተነሳ ምንም ዓይነት በረራ እንዳነበርም ተዘግቧል። የኮሎኝ - ቦን አውሮፕላን ጣቢያም ምንም ዐይነት የመንገደኞች አገልግሎት ያለመኖሩን፤ የሙኒክ አውሮፕላን ጣቢያ በበኩሉ ‘እጅግ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የበረራ መርሃ ግብሮች ብቻ ተፈጻሚ ይሆናሉ’ ሲል ለተጓዦች አስታውቆ ነበር።

በጀርመኑ የአውሮፕላን ጣቢያዎች ማኅበር ግምት መሰረት፤ በጠቅላላው ከ3ሺሕ 500 በላይ በረራዎች ሲሰረዙ፤ ቁጥራቸው 560 ሺሕ የሚጠጉ መንገደኞች የጉዞ መስተጓጎል ገጥሟቸዋል። በሌላ ተዛማች ዜና፡ ስለ ሰኞው የሥራ ማቆም አድማ ዕቅድ ባለፈው ዐርብ አስቀድሞ ያስታወቀው የሠራተኞች ማኅበር፣ ‘ርምጃው ውጤታማ እንዲሆን’ ሲል ትላንት እሐድ ሌላ አጭር ማሳሰቢያ ከሰጠ በኋላ፤ በሃምቡርግ አውሮፕላን ጣቢያ የሥራ ማቆም አድማ ማድረጉም ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG