በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዚምባብዌ ከእርሻ መሬታቸው የተባረሩ ነጭ ገበሬ


ሮበርት ስማርት
ሮበርት ስማርት

በቅርቡ ሥልጣናቸውን የለቀቁት የዚምባብዌ ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ ከሁዳዶቻቸው/ከመሬታቸው/ ካባረሩዋቸው ነጮቹ ገበሬዎች መካከል የመጀመሪያ ትናንት ሃሙስ ወደመሬታቸው ተመልሰዋል።

በቅርቡ ሥልጣናቸውን የለቀቁት የዚምባብዌ ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ ከሁዳዶቻቸው/ከመሬታቸው/ ካባረሩዋቸው ነጮቹ ገበሬዎች መካከል የመጀመሪያ ትናንት ሃሙስ ወደመሬታቸው ተመልሰዋል።

ሮበርት ስማርት ከዋና ከተማዋ ከሃራሬ በስተምሥራቅ ሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሌስበሪ ከተማ ወደሚገኘው እርሻ መሬታቸው ሲሄዱ የጦር ሰራዊት አጃቢ አግኝተዋል።

እሳቸው አጃቢ ጠይቀው ሳይሆን ወታደሩ ባጠገባቸው በመኪና ሲያልፍ ዕርዳታ ይፈልጉ እንደሆን ጠይቁዋቸው አጅቡዋቸው እንደሄደ ተገልጧል።

ሮበርት ስማርት ሲደርሱ በሁዳዱ ላይ ለበርካታ ትውልዶች ይሰሩ የነበሩ እና እነሱም ከነጩ ገበሬ ጋር አብረው ከመሬቱ ላይ የተባረሩ ጥቁሮች ገበሬዎች እያለቀሱ የሞቀ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አዲሱ የዚምባቡዌ ፕሬዚደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ባንድ ወቅት ባለጸጋ የነበረችውን ሃገር ኢኮኖሚ እንዲያገግም እንዳንዶቹን የቀደሙትን ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤን የመሬት ይዞታ ለውጥ ርምጃዎች እሰርዛለሁ ሲሉ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG