በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ የኦሚክሮን መስፋፋት እያሰጋ ነው


የህክምና ባለሞያዋ በዴንቨር ሰዎች ከመኪናዎቻቸው ሳይወርዱ የኮቪድ-19 ምርመራ እያደረጉላቸው፣ ዴንቨር፣ እአአ ዴሴምበር 30/2021
የህክምና ባለሞያዋ በዴንቨር ሰዎች ከመኪናዎቻቸው ሳይወርዱ የኮቪድ-19 ምርመራ እያደረጉላቸው፣ ዴንቨር፣ እአአ ዴሴምበር 30/2021

ሜሪላንድ ኦሃዮና ዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛዎቹ ናቸው

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ከፍተኛው ፍጥነት እየተስፋፋ ባለው የኦሚክሮን ቫይረስ ሳቢያ በመጭው ሳምንት አሜሪካውን የተዛባ ቀውስ ሊገጥማቸው ይችላል ሲሉ በድጋሚ አስጠነቀቁ፡፡

ባለሥልጣናቱ በሁለት ቀን የታየው ከፍተኛ ቁጥር ከእስከ ዛሬዎቹ የላቀ መሆኑን ገልጸው፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ 18 ክፍለ ግዛቶች ከፍተኛውን የተጋላጭ ቁጥር ማስመዘገባቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል ሜሪላንድ፣ ኦሃዮና ዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተጋላጮች ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ በማድረግ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙ መሆኑን በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

በቅርቡ በወጣው የቴክሳስ ዩኒቨርስቲ ጥናት እኤአ ከጥር 18 እስከ የካቲት 3 ያለው ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ሊመዘገብበት የሚችል ጊዜ መሆኑን አመልክቷል፡፡

እስካሁን 62 ከመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን የሞደርና ወይም የፋይዘርን ክትባት አንዱን ወይ ሁለቱን የወሰዱ ቢሆንም፣ የማጠናከሪያውን ክትባት የወሰዱት አንድ ሦስተኛ አሜሪካውያን ብቻ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ በወረርሽኙ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 823ሺ743 ሲሆኑ ፣ በኦሚክሮን ቫይረስ የሞቱት ምን ያህል እንደሆኑ እስካሁን አለመታወቁ ተነገሯል፡፡

XS
SM
MD
LG