በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒው ዮርክ ኦሚክሮን ቫይረስ በተለያዩ ሰዎች ላይ ታየ


ኒው ዮርክ ውስጥ ከተንቀሳቃሽ የኮቪድ-19 ክትባት ማጠናከሪያ ጣቢያ ክትባት ለመውሰድ ወረፋ ሲጠባበቁ
ኒው ዮርክ ውስጥ ከተንቀሳቃሽ የኮቪድ-19 ክትባት ማጠናከሪያ ጣቢያ ክትባት ለመውሰድ ወረፋ ሲጠባበቁ

ኒው ዮርክ ውስጥ ኦሚክሮን ለተባለው የኮቪድ-19 ቫይረሰ ዝርያ የተጋለጡ 5 ሰዎች መገኘታቸውን የጤና ባለሥልጣናት ማረጋገጣቸውን የኒው ዮርክ ገዥ ካቲ ሆቹል ትናንት አስታወቁ፡፡

ባለሥልጣንዋ “የሚያሰጋ ነገር ኖሮ ሳይሆን የደረሰንን መረጃ ለህዝቡ ማሳወቅ ስላለብን ብቻ ነው” ብለዋል፡፡

የጤና ባለሥልጣናቱ ቫይረሱ ኒው ዮርክ ውስጥ በተለያዩ ሰዎች ላይ መታየቱን ገልጸው ኒው ዮርክ ውስጥ ባላፈ ወር በተካሄደ የንግድ ትርኢት ተካፍሎ ወደ ሚኒሶታ ግዛት የተመለሰ አንድ ሰው ላይም የተገኘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ በተካሄድ ምርመራ አምስት ሰዎች ቫይረሱ የታየባቸው ሲሆን በተለይ ሎንግ አይላንድ ነዋሪ የሆነና በቅርቡ ከደቡብ አፍሪካ በመጣ ሰው ላይ መታየቱንም አስረድተዋል፡፡

ይህ ዜና የመጣው በዩናይትድ ስቴትስ የመጀሪያው የኦሚክሮን ቫይረስ የታየበት ሰው በካሊፎርኒያ መገኘቱን በተነገረ ማግስት ነው፡፡ ባለሥልጣናቱ ለዚህ ሁሉ መድሃኒቱ የማጠናከሪያውን ክትባት ጨምሮ ሁሉንም ክትባቶችን አሟልቶ መውሰዱ መሆኑን አሳሰበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG