በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትልቁ የሶማሊያ የቴሌኮም ኩባኒያ በቦምብ ፍንዳታ ጉዳት ደርሶበታል


ፎቶ ፋይል፦ የአልሻባብ
ፎቶ ፋይል፦ የአልሻባብ

ትልቁ የሶማሊያ የቴሌኮሙኒኬሽ ኩባኒያ ሆርሙድ ቴሌኮም ጋልሙዱግ ክፍለ ግዛት ውስጥ በደረሰው ፍንዳታ በዚያ ያለው ማዕከል እና አንደኛው የቴሌኮሙኒኬሽን ማማ (ታወር) መውደሙን አስታወቀ።

ውድመቱ የደረሰው ትናንት ጋልሙዱግ ውስጥ በምትገኘው ካያብ የተባለች መንደር በደረሰው በመኪና ላይ የተጫነ ቦምብ ፍንዳታ መሆኑን ኩባኒያው አስታውቋል።

በደረሰው ውድመት የተነሳም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በተንቀሳቃሽ ስልኮች ክፍያዎችን የሚፈጽሙበት አገልግሎት እንደተቋረጠባቸው ሆርሙድ ቴሌኮም አመልክቷል።

"ማዕከሉን መልሰን ገንብተን ለአካባቢው የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት እንቀጥላለን" ሲል ኩባኒያው ትናንት ባወጣው መግለጫ ቃል ገብቷል።

አልሻባብ ትናንት ሰኞ በድረ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ካዪብ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥቱ የጦር ካምፕ ላይ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃት ማድረሱን እና እስከትሎም ታጣቂዎቹ ተኩስ ከፍተው 37 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቆ የነበረ ሲሆን በነጻ ምንጭ አልተረጋገጠም።

የሶማሊያ መንግሥት የጭነት መኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ጥቃት መድረሱን አረጋጋጦ "ወታደሮቻችን የጦር ካምፑ ላይ ጥቃት የከፈቱትን የአልሻባብ ታጣቂዎች አሸንፈዋቸዋል" ብሏል።

XS
SM
MD
LG