በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
የተመድ የሰብዓዊ መብት ባለሞያዎች ቡድን የሥራ ዘመን እንዲራዘም የኦሮሞ ቅርስ ማኅበር ጠየቀ

የተመድ የሰብዓዊ መብት ባለሞያዎች ቡድን የሥራ ዘመን እንዲራዘም የኦሮሞ ቅርስ ማኅበር ጠየቀ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የኦሮሞ ቅርስ አመራር እና ተሟጋች ማኅበር ፣ የሥራ ዘመኑ በዚህ ዓመት የሚያበቃውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለኢትዮጵያ የተቋቋመው የሰብአዊ መብት ባለሞያዎች ዓለም አቀፍ ኮሚሽን የሥራ ዘመኑ እንዲራዘም ጥሪ አድርጓል።

በመላ ኢትዮጵያ የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር የዓለም አቀፉ ኮሚሽን “ብቸኛ ተአማኒ ድርጅት ነው” ያለው ማኅበሩ፣ የሥራ ዘመኑ እንዲራዘም ከአሜሪካ ኮንግረስ አባላት፣ ከአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ ዓባለት እንዲሁም ከተመድ ባለሥልጣናት ጋራ በመገናኘት የኮሚሽኑ የሥራ ዘመን እንዲራዘም መቀስቀሱን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ያለፈው ዓመት መስከረም ሪፖርት በሰሜን ኢትዮጵያ ላይ ያተኮረ እንደነበር ያስታወሰው የማኅበሩ መግለጫ፣ የኮሚሽኑ ሥራ ወደ ተቀረው የሃገሪቱ ክፍል እና ወደ ኦሮሚያም እንዲስፋፋ ከኮሚሽኑ ጋር ባለፈው ዓመት ጀኒቫ ላይ በተወያየበት ወቅት አጽንኦት መስጠቱን አመልክቷል።

በኦሮሞ ሲቪሎች ላይ በተለይያዩ ኃይሎች ጥቃት ይደርሳል ያለው ማኅበሩ፣ ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ሥራዉን ለማስፋፋት መስማማቱ አስድስቶት እንደነበር ጠቁሟል።

“በሀገሪቱ ሁከት በመበራከት ላይ ባለበት ሰዓት እና በኦሮሞዎች ላይ የጥላቻ ንግግር በተበራከተበት ሰዓት የኮሞሽኑ የሥራ ዘመን ላይታደስ የመቻሉ ጉዳይ አሳዛኝ ነው” ሲል መግለጫው አመልክቷል።

በመደረግ ላይ ያለው የሽግግር ፍትሕ ጥረት ሥራ በአብዛኛው የሁከቱ ፈጻሚ ነው ሲል ለከሰሰው መንግሥት መተው እንዳሳሰበው ማኅበሩ ገልጿል። መንግሥት የኮሚሽኑን ምርመራ እንዲቀጥል እንዲፈቅድ ጥሪ ያደረገው ማኅበሩ፣ ለሽግግር ፍትህ እና እርቅ ተአማኒ እና ገለልተኛ ነው ሲል የገለጸው ኮሚሽን አስፈላጊ ነው ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG