በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦነግ አመራር አባላት ስለ ውዝግቡ ምን ይላሉ?


ሰሞኑን በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር አባላት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ በድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እና በምክትላቸው አቶ አራርሶ ቢቅላ መሪነት ተለያይተው የቆሙት የአመራር አባላት በየፊናቸው በሚያወጧቸው መግለጫዎቹ ሲወቃቀሱ መቆየታቸውም ይታወቃል፡፡ አሁን ምን ደረጃ ላይ ናቸው?

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የህግ፣ የሥነ ሥርዓትና ቁጥጥር ኮሚቴ ፣ በድርጅቱ ህገ ደንብ መሰረት ጉዳዩን መርምሮ እልባት ለመስጠት እየሠራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች በገጠሙ ጊዜ ሁኔታው በጠቅላላው ጉባኤ የሚዳኝ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ በዚህ ዙሪያ ግራን ቀኝ ያሉትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባን እንዲሁም ጊዚያዊ ቃል አቀባይ አቶ መሀመድ ረጋሳን ጨምሮ የድርጅቱን የህግ የሥነሥር ዓትና ቁጥጥር ኮሚቴ ኃላፊን አቶ ዓለማየሁ ዲሮን አነጋግረናቸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኦነግ አመራር አባላት ስለ ውዝግቡ ምን ይላሉ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:24:44 0:00


XS
SM
MD
LG