የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ያዘጋጀው የእርቀ-ሰላም መድረክ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይም የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መሪዎችን ጨምሮ ሌሎች በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሣትፈዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ሰብሳቢ አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ፥ “ሃገራችንን የምንጠብቀው እኛ ነን፤ የሃገራችን ጉዳይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አይደለም፤ የእኛ ጉዳይ ነው፤ የሃገራችን ሰላም ጉዳይ ሁላችንንም ያገባናል” ብለዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ