በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦነግ አመራሮቹ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና የት እንደታሰሩ እንደማያውቅ ገለፀ


የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ቢሮ በበኩል የታሰሩበት እንደሚታወቅ ፍርድ ቤት እንደቀረቡም አስታውቋል

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ ከፍተኛ አመራሮቹና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ ከታሰሩ አሥራ አምስት ቀናት ቢያልፉም ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

ግለሰቦቹ ስለሚገኙበት ሁኔታ ፓርቲው ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቻቸውም ጭምር እንደማያውቁ ተናግረዋል።

የኦሮምያ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጂብሪል መሐመድ በበኩላቸው ግለሰቦቹ የት እንደሚገኙ እንደሚታወቅ ገልፀዋል። “ታስሮ ፍርድ ቤት ያልቀረበ፣ወይንም የምርመራ ውጤቱ ያልተጀመረ፣ ወይንም ተመርምሮ መዝገብ ያልተደራጀበት ሰው የለም” ብለዋል።

ግለሰቦቹ የታሰሩት ኢትዮጵያ ውስጥ በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋት፣ አካል መጉደል እና ንብረት መውደም ተጠርጥረው እንጂ ከፖለቲካ ፓርቲ ሥራቸው ጋር በተያያዘ እንዳልሆነም ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኦነግ አመራሮቹ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና የት እንደታሰሩ እንደማያውቅ ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:44 0:00


XS
SM
MD
LG