በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቶ አብዲ ረጋሳ የት እንዳሉ እንደማያውቁ ጠበቆቻቸውም ፓርቲያቸውም ተናገሩ


በፍርድ ቤት በነፃ የተለቀቁት አቶ አብዲ ረጋሳ ዳግም ተይዘው ያሉበት አይታወቅም ጠበቃቸው። የኦነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አብዲ ረጋሳ በኦሮምያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነጻ ከተለቀቁ በኋላ ዳግም መታሰራቸው ተነግሯል። ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ፣ ባለፈው ሀሙስ የኦሮምያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት ወንጀል ነጻ ናቸው ብሎ ቢለቃቸውም፣ ወዲያውኑ የመንግሥት የደህንነት ሰዎች ባሏቸው ሰዎች ተወስደዋል ብለዋል።

አቶ ለሚ ገመቹ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጊዜያዊ ህዝብ ግንኙነት ተወካይ በበኩላቸው፣ አሁንም አቶ አብዲ ወዴት እንደተወሰዱ የሚታወቅ የለም ብለዋል። የመንግሥት የጸጥታ ኃላፊዎች ስለአቶ አብዲ መሰወር መልስ እንዲሰጡ የተደረገ ጥረት አልተሳካም።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አቶ አብዲ ረጋሳ የት እንዳሉ እንደማያውቁ ጠበቆቻቸውም ፓርቲያቸውም ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:57 0:00


XS
SM
MD
LG