በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ገልገሎ ጉፋ ተከላከሉ፤ ኦልባና ሌሊሣ በእሥር ቤት ደረሰብኝ ያሉትን በደል ለዳኛ አሰሙ


ፌደራል አቃቢ ሕግ በእነ በቀለ ገርባ መዝገብ ክስ ከመሠረተባቸው ዘጠኝ ሰዎች መካከል የዘጠነኛው ተከሣሽ የመከላከያ ምሥክሮች ቃል ተሰምቷል፡፡

ሁለተኛው ተከሣሽ አቶ ኦልባና ሌሊሣ እሥር ቤት ውስጥ መደብደባቸውን ለችሎት ይፋ አድርገዋል፡፡

በዘጠነኛው ተከሣሽ አቶ ገልገሎ ጉፋ ላይ አቃቢ ሕግ ሁለት ክስ መሥርቶባቸዋል፡፡

አንደኛው ክስ የሃገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት ወንጀል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተደብቆ ተገኘ በተባለው መትረየስ እና ባዶ ሠንሰለት ምክንያት “የተንኮል ድርጊቶችን ግዙፍ በሆነ ዓይነት ማሰናዳት ወንጀል” የሚል ነበር፡፡

አቃቢ ሕግ ቀደም ሲል ከክሱ አኳያ ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰውና የሠነድ ማስረጃዎች አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተከሣሽ እንዲከላከሉ ወስኗል፡፡

በዚህም መሠረት ዘጠነኛው ተከሣሽ አቶ ገልገሎ ለፍርድ ቤቱ ዛሬ በሰጡት ቃል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባል የነበሩት አቃቢ ሕግ በክሡ ላይ እንዳለው ከ1993 እስከ 2003 ዓ.ም ሳይሆን ከ1984 እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ እንደነበረ ገልፀዋል፡፡

በኦነግ ውስጥም በቡድን መሪነት ብቻ ሳይሆን ከዚያም ከፍ ባለ ኃላፊነት መሥራታቸውን ተናግረዋል፡፡

በ2002 ዓ.ም ግን ከሌሎች ከኦነግ አባላት ጋር ሆነው እጃቸውን ለመንግሥት ሲሰጡም የኦነግን ዓላማ ኮንነው እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በችሎቱ ፊት ዛሬ የቀረቡት አቶ ኦልባና ሌሊሣ “በእሥር ቤቱ ውስጥ በደል ተፈፅሞብኛል” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አቤት ብለዋል፡፡

ጉዳዩ ለሰኔ 12/2004 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡

ዝርዝሩን ከመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG