በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ እየተካሄደ ባለው ሰልፍ ለቀረበው የሰላም ጥሪ የክልሉ መንግሥትና ታጣቂ ኃይሉ ምላሽ ሰጥተዋል


በኦሮሚያ የተካሄደው ሰልፍ
በኦሮሚያ የተካሄደው ሰልፍ
በኦሮሚያ እየተካሄደ ባለው ሰልፍ ለቀረበው የሰላም ጥሪ የክልሉ መንግሥትና ታጣቂ ኃይሉ ምላሽ ሰጥተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:25 0:00

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ቄለም ወለጋ፣አርሲ፣ጉጂ ዞኖችና የተለያዩ ወረዳዎች ባለፈው ሳምንት በተካሄዱ ሰልፎች ላይ ለቀረበው የሰላም ጥሪ፣ የክልሉ መንግሥታ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች የየበኩላቸውን ምላሽ ሰጥተዋል።

የክልሉ መንግሥት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው የጹሑፍ መግለጫ፣ የሰላማዊ ሰልፍን ጥሪ እንደሚቀበል አስታውቋል። የክልል መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ኃይሉ አዱኛ ሰልፎቹን አስመልክተው፣ መንግሥታቸው የሕዝቡን ጥሪ እንደሚቀበልና በሩ ለሰላም ክፍት መኾኑን ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

ኖርዌይ የሚገኙትና የታጣቂ ቡድኑ አማካሪ መኾናቸውን የሚናገሩት፣አቶ ጅሬኛ ጉደታ የሰላም ጥሪው በትክክለኛ መንገድ በኅብረተሰቡ የቀረበ ነው ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል። "እኛ ኅብረተሰቡም ጥሪ ሳያቀርብልን ራሳች እውነተኛ ሰላም በሀገሪቱ እንድ ሰፍን የበኩላችን እንጥራለን ነገር ግን አንድ ወገን ብቻውን ሰላም ስለፈለገ ብቻ ማምጣት አችልም” ብለዋል።

በሁለቱ ቀናት በተካሄዱ ሰልፎች ላይ የተገኙና የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አንዳንዶቹ ተሳታፊዎች ሰልፉ በመንግሥት አስተባባሪነት እንደተዘጋጀ ሲናገሩ፣ ሌሎች ደግሞ "መንግሥትና ታጣቂው ቡድን ሰላም እንዲያወርዱ ለመጠየቅ በኅብረተሰቡ የተዘጋጀ ነው" ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ኃይሉ አዱኛ "መንግሥት ሰልፉን በማስተባበር ውስጥ እጁ የለበትም" ብለው ነበር። አቶ ጅሬኛ ጉዳታ የሰላም ጥያቄ እያቀረበ ያለው የትኛው የኅብረተሰብ የሚለው ላይ ጥያቄ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG