የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጽሕፈት ቤት፣ መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ጋራ ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ወደ ተዘጋጁላቸው ማዕከላት እየገቡ መኾኑን አስታወቀ።
ቢሮው በማኅበራዊ ትስስር ገፆቹ ባወጣው መግለጫ፣ በተለይ በምዕራብ ሸዋና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነፃነት ታጣቂዎች የሰላሙን ጥሪ ተቀብለው ወደተዘጋጀላቸዉ የመቀበያ ቦታዎች እየገቡ እንደኾነም ጠቁሟል። የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ነዋሪዎችም፣ ለታጣቂዎቹ አቀባበል እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል።
ይህን በተመለከተ ከመንግሥትና ከኦሮሞ ነፃነት ታጣቂዎች ምላሸ አዛዦች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳም።
መድረክ / ፎረም