በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትሷ ኦሃዮ ክፍለ ሃገር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ


በዩናይትድ ስቴትሷ ኦሃዮ ክፍለ ሃገር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ በጊዜያዊነት ለመሙላት በተካሄደውና ብርቱ ትኩረት የሳበው ልዩ ምርጫ ተፎካካሪዎቹ ያገኙት ድምጽ አሸናፊውን ለመለየት በሚያዳግት ደረጃ እጅግ የተቀራረበ ሆኗል።

በዩናይትድ ስቴትሷ ኦሃዮ ክፍለ ሃገር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ በጊዜያዊነት ለመሙላት በተካሄደውና ብርቱ ትኩረት የሳበው ልዩ ምርጫ ተፎካካሪዎቹ ያገኙት ድምጽ አሸናፊውን ለመለየት በሚያዳግት ደረጃ እጅግ የተቀራረበ ሆኗል። ሪፖብሊካኖችና ዲሞክራቶች የኦሃዮውን ምርጫና በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የሚካሄዱ ቅድመ መርጫዎችን በሚቀጥለው ኅዳር ወር ስለሚካሄዱት ሀገርቀፍ ምርጫዎች ፍንጭ ይሰጣሉ በሚል በቅርበት እየተከታተሉ ናቸው።

በኦሃዮው ልዩ ምርጫ በሁሉም የምርጫ ወረዳዎች የተሰጠው ድምፁ ገብቶ ሪፖብሊካኑ ትሮይ ባልደርሰን ዲሞክራቱን ዳኒ ኦካነርን በ1700 ገደማ ድምፅ ብልጫ ይመሯቸዋል። ይሁን እንጂ በጊዚያዊ የመምረጫ ካርድ ድምፅ የሰጡ ከሦስት ሺህ አራት መቶ በላይ መራጮች እና በአካል ሳይገኙ ድምፅ የሰጡ ደግሞ አምስት ሺህ መራጮች እንዳሉ ባለሥልጣናቱ ገልፀዋል።

በክፍለ ሀገርዋ ህግ መሰረት ምርጫው ከተከናወነ ከአሥራ አንድ ቀን በፊት ድምፅ ቆጠራ እንደማይጀመር አመልክተዋል። በኅዳር ወር በሚካሄደው ምርጫ 435ቱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ መቀመጫዎች ከመወሰኛው 100 ወንበሮች ሰላሳ አምስቱ ከሃምሳው የአገረ ገዢ ሥልጣኖች ሰላሳ ስድስቱ ለውድድር ይቀርባሉ።

ዲሞክራቶች ሁለቱንም ሸንጎዎች ለመቆጣጠር ከተወካዮች ምክር ቤቱ ሃያ ሦስት ከመወሰኛው ደግሞ ሁለት መቀመጫዎች ማሸነፍ ይኖርባቸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG