በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ እስላማዊ አክራሪዎች ጥቃት ሰነዘሩ፣ ምርጫ አስፈጻሚዎች ታገቱ


የናይጄሪያ ምርጫ
የናይጄሪያ ምርጫ

በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ በእስላማዊ አክራሪዎች የተሰነዘረውን ጥቃት የጸጥታ ኃይሎች መመከታቸው ሲነገር፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በርካታ የምርጫ አስፈጻሚዎች መጠለፋቸው ታውቋል።

ለአገረ-ገዢነት የተደረገው ምርጭ ውጤት እየተንጠባጠበ በመገለጽ ላይ ሲሆን፣ በሌጎስ ግዛት ተቀማጩ አገረ ገዢ ደግመው ሳይመረጡ እንዳልቀረ ተዘግቧል።

በአንዳንድ ቦታዎች ሁከት ተከስቶ እንደነበር መረጃ እንደደረሳቸውና ጉዳዩን እያጣሩ መሆኑን የምርጫ ቦርድ ኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ትናንት አስታውቀዋል።

አንድ የምርጫ አስፈጻሚ ሲገደል፣ ሌሎች ደግሞ ወከባና እንግልት ሲገጥማቸው አንዳንዶች ደሞ ለሆስፒታል በቅተዋል ብለዋል ቃል አቀባዩ።

36 ከሚሆኑት የናይጄሪያ ግዛቶች 28 የሚሆኑት ቅዳሜ ዕለት የአገረ-ገዢ ምርጫ ያከናወኑ ሲሆን፣ አንድ ሺህ በሚሆኑ የምርጫ ክልሎች ደግሞ የሕዝብ ተወካዮች ምርጫ ተካሂዷል።

የናይጄሪያ ሕገ-መንግሥት ለአገረ ገዢዎች ከፍተኛ ሥልጣንና ያለመከሰስ መብት የሚሠጥ ሲሆን፣ ይህም በግዛታቸውም ሆነ በፌዴራል ደረጃ ከፍተኛ ተጽእኖ ያላቸው ያደርጋቸዋል።

የቅዳሜው ምርጫ የተካሄደው በቅርቡ የተደረገውንና የገዢው ፓርቲ ተወካይ ቦላ ቲንቡ አሸናፊ የሆኑበትን ውጤት ተቃዋሚዎች እንደማይቀበሉ መግለጻቸውን እየቀጠሉ ባለበት ወቅት ነው።

በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት በእስላማዊ መንግሥት የሚደገፉ አክራሪዎች የምርጫ ቆጠራ በሚካሄድበት ማዕከል ላይ ጥቃት የሠነዘሩ ሲሆን፣ የጸጥታ ኃይሎች ጥቃቱን መክተው በርካቶችን እንደገደሉ የአካባቢው ባለሥልጣናትና ነዋሪዎች ተናግረዋል ሲል አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG