በሙስና ተወንጅለው እሥር ላይ የሚገኙት የሳውዲው ልዑል ሚተብ ቢን አብዱላህ በቢልዮን ዶላር የተገመተ ገንዘብ የስምምነት ክፍያ መለቀቃቸውን የሳውዲ አረቢያ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ባንድ ወቅት ግንባር ቀደሙ የአልጋ ወራሽ ተደርገው ይታዩ የነበሩትና የአገሪቱ ልዩ ብሔራዊው ጦር አዛዝ የነበሩት የሟቹ ንጉስ አብዱላ ልጅ ከ20 ቀናት በላይ እሥር በኋላ በትላንትናው ዕለት ነው ከእሥር የተለቀቁት።
ልዑሉ በከፊል የሠላሳ ሁለት ዓመቱን ልዑል አልጋ ወራሽ ቢን ሳልማንን የአገሪቱን ሥልጣን ጠቅልሎ የመያዝ አቅም ለማጠናከር የታለመ ጭምር ተደርጎ በተወሰደ መጠነ ሰፊ የሙስና ምርመራ ሳቢያ ከታሰሩ በርካታ ልዑላን ሚንስትሮች እና ታዋቂ የንግድ ሰዎች አንደኛው ናቸው።
ልዑል አብዱላህ ከመንግሥት ጋር የሚደረግ የሥራ ተቋራጭ ለገዛ ድርጅታቸው መስጠትና የሌሉ ሰዎችን በሃሰት እንደተቀጠሩ አድርጎ ማቅረብ የሚሉትን ጨምሮ የገንዘብ ምዝበራ ፈፅመዋል በሚሉ ወንጀሎች ነው፣ የተከሰሱት።
የተጠየቁትን ገንዘብና ንብረት ለመንግሥት ማስረከብን ጨምሮ ከእሥር መለቀቅ የሚያስችሉ ተመሳሳይ ስምምነቶችን ከተቀሩት ተመሳሳይ ክስ ከቀረበባቸው ልዑላን፣ ሚንስትሮች እና ታዋቂ የንግድ ሰዎች ጋርም በመፈፀም ላይ መሆናቸውን የሳውዲ አረቢያ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ