ዋሺንግተን ዲሲ —
በሶማሊያ ፑንትላንድ አስተዳደሮች ባጨቃጫቂው የሰሜን ሡል ግዛት እንደገና የጀመሩትን ውጊያ እንዲያቆሙ የሶማሊያ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አስተላልፏል።
ተፋላሚዎቹ ወገኖች ቅዱሱን የሙስሊሞች የረመዳን ወር ፆም መጀመር ምክንያት በማድረግ በአስችኳይ ተኩስ ሊያቆሙ ይገባል ሲሉ - ፕሬዘዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ተናግረዋል።
በሱማልያ ሕዝቦች መካከል በዚህ ቅዱስ ወር ወቅት ሌላ ደም መፋሰስ ማየቱ ያሳዝናል ያለው የፕሬዛዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ መግለጫ የአስተዳደሮቹ የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎች - የተኩስ አቁም ድርድሮችን እንዲሸመግሉ ጥሪ ያቀርባል።
በሶማሊያ ፑንትላንድ መካከል አዲስ ባገረሸው ውጊያ በትንሹ ስድሥት ወታደሮች ከሁለቱም ወገን መገደላቸውን በርካታ ምንጮች ገልፀዋል። ተኩሱን በመጀመር አንዱ ሌላውን ይወነጅላል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ