አዲስ አበባ —
መንግሥት ለምርጫ ዝግጅት ከማድረጉ በፊት በእስር የሚገኙ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትና አመራሮችን መፍታት አለበት ሲል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አሳሰበ።
የፓርቲው ሊቀ-መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፁት የፖለቲካ ምህዳሩ በመስፋት እውነተኛ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ እንዲወለድ መንግሥት የፖለቲካ ፓርቲ እስረኞችን መፍታት አለበት ብለዋል።
በዚህ ዙርያ ከብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።