ዋሺንግተን ዲሲ —
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ግጭት ሽሽትና በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለመታደገ የ280 ሚሊዮን ዶላርስ አስቸኳይ ዕርዳታ ጠየቀ።
የመንግታቱ ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ መስተባበሪያ ድርጅት/ኦቻ/ በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው መረጃ በሶማሊያና ኦሮምያ ክልል የድንበር አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎችን በፍጥነት ለመርዳት የሚያስችል አቅም መጠናከር አለበት ብሏል። ለዚህ የሚውል 280 ሚሊዮን ዶላርስ የረድዔት ጥሪም ቀርቧል።
የኦቻ ቃል አቀባይ የንስ ላርከ ለሁለት ተደጋጋሚ የምርት ወቅቶች የተከሰተው ድርቅ ከግጭት ጋር ተዳምሮ የተፈናቃዮችን ኑሮ በእጅጉ የከፋ አድርጓል ብለዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ