በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካዊው አቀንቃኝ ቶኒ ቤኔት በሞት ተለየ


አሜሪካዊው አቀንቃኝ ቶኒ ቤኔት በሞት ተለየ
አሜሪካዊው አቀንቃኝ ቶኒ ቤኔት በሞት ተለየ

በአሜሪካ፣ ቆየት ባሉ አገርኛ ዘፈኖች የሚታወቀው ቶኒ ቤኔት፣ ኒው ዮርክ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እንዳለ፣ በ96 ዓመቱ ከዚኽ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

ዐዲስ የሙዚቃ ደረጃን ለመፍጠር ተሰጥኦው የነበረው ቶኒ ቤኔት፣ ዛሬ ዐርብ ማረፉን፣ የአቀንቃኙ የሕዝብ ግንኙነት ተወካይ አስታውቀዋል።

በሕይወቱ ማድረግ የሚመኘው፣ “ለጊዜው ብቻ ከፍተኛ ተሰሚነት ያለው ዘፈን ማውጣት ሳይኾን፣ ሠርክ ዐዲስ የኾነ ተደማጭ ዜማ መሥራት” እንደኾነ ቶኒ ቤኔት በተደጋጋሚ ሲገልጽ ተሰምቷል።

የእርሱ ዘመን አቀንቃኝ የነበረው ፍራንክ ሲናትራ፣ በአንድ ወቅት ለ“ላይፍ” መጽሔት በሰጠው አስተያየት፣ ቶኒ ቤኔት፥ በሙዚቃው ዓለም ምርጥ ዘፋኝ እንደኾነ መስክሮለታል።

ቶኒ ቤኔት፣ በምን ምክንያት እንደሞተ ባይታወቅም፣ ከሰባት ዓመታት በፊት፣ በ“አልዛይመር” ወይም የመርሳት በሽታ እንደተያዘ ተነግሮ ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG