WASHINGTON, D.C. —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ከትላንት በስቲያ ሰኞ በአፍሪካ ህብረት ዋና ጽሕፈት ቤት አዳራሽ ተገኝተው ያሰሙት ንግግር ሰፊና ብዙ ርዕሶችን የሸፈነ ነው። ስለ ዲሞክራሲ አስፈላጊነት፥ ሽብርተኝነትን በጋራ ስለመዋጋት፥ ስለ አካባቢ ደህንነት ጥበቃ በስፋት ተናግረዋል። በተለይ አህጉሪቱ ውስጥ እንደ ነቀርሣ በሽታ ሥር ሰድዶ ሕዝቦቿን በከፍተኛ ደረጃ እያደዀየ ስላለውም የሙስና ችግር አውስተዋል።
የምሽቱ “ዲሞክራሲ በተግባር ፕሮግራም” ፕሬዘዳንት ኦባማ ስለ ሙስና ያደረጉትን ንግግር በኢኮኖሚ ባለሞያ ያስተነትናል።