በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለሥራ ፈጠራ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደምታወጣ ኦባማ አስታወቁ


ለተመሣሣይ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጥያቄው የኬንያ ጥያቄ አይደለም - ኡሁሩ ኬንያታ

ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም ዙሪያ ለሚከናወኑ የሥራ ፈጠራ ክንዋኔዎች የአንድ ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ-ነዋይ እንደምታፈስስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዛሬ አታውቀዋል፡፡

ኦባማ ይህንን የመንግሥታቸውን ሃሣብ ይፋ ያደረጉት ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ እየተካሄደ ላለው ለስድስተኛው የዓለም የሥራ ፈጠራ ጉባዔ ንግግር ባደረጉበት መድረክ ላይ ነው፡፡

ባለፈው የሞሮኮ ጉባዔ በተገባው ቃል መሠረት ሥራ ፈጠራን፣ በዓለም ዙሪያ አዳዲስ ሥራዎችን ለመክፈት፣ ለማሳለጥ፣ ለማቀላጠፍና ለማስፋት እገዛ ይውላል የተባለው የገንዘብ ድጋፍ ምንጭ ባንኮች፣

ድርጅቶች፣ በጎ ፍቃደኞች መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

ከታሰበው በላይ ገንዘብ መገኘቱን የገለፁት ፕሬዚዳንት ኦባማ ከገንዘቡ ግማሹ የሚፈስሰው ሴቶችና ወጣቶች በሚፈጥሯቸው ሥራዎች ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስና ኬንያ ዓለምአቀፍ ሽብር የደቀነውን አደጋ ለመከላከል በጋራ ይቆማሉ ሲሉ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ሆነው መግለጫ የሰጡት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስታውቀዋል፡፡

የሶማሊያውን ፅንፈኛ የሁከት ቡድን አል ሻባብን በመዋጋት ያደረጉትን ጨምሮ “ሥኬታማ ፀረ-ሽብር መደጋገፍ” ያሉት መጠነ ሰፊ የትብብር ግንኙነት በሁለቱ ሃገሮች መካከል መኖሩን ኦባማ አመልክተዋል፡፡

ለበርካታ ዓመታት በዘለቀው የሶማሊያ ብጥብጥ ሳቢያ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገዷ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኬንያን አመስግነዋል፡፡

ኬንያ ውስጥ ሙስናን ለመዋጋት ሚስተር ኬንያታ ላሳዩት ቁርጠኝነትም ኦባማ እንዲሁ አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡

ዜጎችን አዳዲስ ሥራዎችን ከመጀመር ያደናቅፋል ያሉትን ጉቦ መቀበልን ባለሥልጣናቱ እንዲያቆሙም መክረዋል፡፡

የተመሣሣይ ፆታ ግንኙነትን በተመለከተ ከጋዜጠኞቹ ጥያቄ የቀረበላቸው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት አንድ ሃገር በፆታ ዝንባሌና የፍቅር ምርጫቸው ሳቢያ ሰዎችን ማግለል የለባትም ብለዋል፡፡

ለተመሣሣይ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጥያቄው የኬንያ ጥያቄ አይደለም፤ በሕዝባችን ላይ ያለፍላጎቱ የምንጭነው ጉዳይ የለም ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

አሜሪካ ለሥራ ፈጠራ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደምታወጣ ኦባማ አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:43 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG