በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቁም ነገሩ ኦባማ ከመጡ በኋላ የሚያደርጉት ላይ ነው - ርዕዮት ዓለሙ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ኢትዮጵያን መጎብኘት እንደማትቃወም በቅርቡ ከአራት ዓመታት እሥር በኋላ የተፈታችው ርዕዮት ዓለሙ አስታውቃለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ኢትዮጵያን መጎብኘት እንደማትቃወም በቅርቡ ከአራት ዓመታት እሥር በኋላ የተፈታችው ርዕዮት ዓለሙ አስታውቃለች፡፡

መምህርትና ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ የተፈታችው ምናልባት ከፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ጋር ተያይዞ ነው ብላ ታስብ እንደሆነ የተጠየቀችው ርዕዮት ለቪኦኤ በሰጠችው ቃል ይህንኑ ጥያቄ ሌሎችም እንደሚጠይቋት ተናግራ ነገሩ ቢመስልም በሌላ በኩል ደግሞ እርሷ ከተፈታች በኋላና ሰሞኑንም ብዙ የተቃዋሚ መሪዎች እየታሠሩ መሆናቸውን ገልፃለች፡፡

ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የኢሕአዴግን መሪዎች አግኝተውና ሕንፃና መንገድ አይተው የሚመለሱ ከሆነ የኢትዮጵያን እውነተኛ ገፅታ ለማግኘት አይችሉም ያለችው ርዕዮት የሲቪል ማኅበረሰቡን፣ ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚዎችንም ያገኛሉ ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ገልፃለች፡፡

አንቺ ቢጠይቁሽ ምን ትናገሪያለሽ? ስትባልም የፍትሕ ሥርዓቱ መዛባቱን፣ አሜሪካ የምትሰጠው እርዳታ ለታሰበው ጉዳይ መዋል አለመዋሉን እንድትቆጣጠር፣ መገናኛ ብዙኃንን ለማፈን ይውል እንደሆነ እንድትፈትሽ አሳስባቸዋለሁ ብላለች፡፡

“አሁንም አልታሠርም፤ ወይም ጉዳት አይደርስብኝም ብዬ ባስብ ኢሕአዴግን አለማወቅ ይሆንብኛል” ብላለች ርዕዮት አክላ፡፡

ከርዕዮት ዓለሙ ጋር ለተደረገው ውይይት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ቁም ነገሩ ኦባማ ከመጡ በኋላ የሚያደርጉት ላይ ነው - ርዕዮት ዓለሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG