በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ዶናልድ ትራምፕ ሙስሊሞችን አስመልክቶ ያላቸውን አመለካከት አጥብቀው ነቀፉ


ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ትላንት ባልተለመደ ሁኔታ ለፕረዚንትነት የሚወዳደሩት ሪፑብሊካዊ ቢልዮነር ዶናልድ ትራምፕ ሙስሊሞችን አስመልክቶ ያላቸውን አመለካከት አጥብቀው ነቅፈዋል። ትራምፕ በሙስሊሞች ላይ እገዳ እንዲደረግ ያቀረቡትን ሃሳብ አስመልክቶ የትራምፕ ልፍለፋ የዩናይትድ ስቴትስ የጸጥታ ሁኔታን አደጋ ላይ ይጥላል በማለት ነቅፈዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ በኦርላንዶ የተፈጸመውን የጅምላ ግድያን በሚመለከት ከጸጥታ ጉዳይ አማካሪዎች ጋር ተገናኝተው ከተናጋገሩ በኋላ ዶናልድ ትራምፕ ሙስሊሞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ እገዳ እንዲደረግ ያቀረቡትን ሃሳብን አጥብቀው ነቅፈዋል።

“መላ ሙስሊሞችን በአንድ አይን በማየት ወጥመድ ውስጥ ገብተን ከመላ ሀይማኖቱ ጋር ጦርነት እንደገባን አድርገን የምናቀርብ ከሆነ የነሱን የአሸባሪነት ተግባር እየፈጸምንላቸው ነው ማለት ነው።”

ፕረዚዳንት ኦባማ ይህን ያሉት ፕራምፕ ባለፈው ሰኞ ለተናገሩት ምላሽ ነው። የኦባማ አስተዳደርና የሂለሪ ክሊንተን ፖሊሲዎች አሸባሪዎቹን ረድተዋል ሲሉ ትራምፕ ነቅፈው ነበር።

ፔንሲልቬንያ ውስጥ የምርጫ ዘመቻ በማካሄድ ላይ የነበሩት ዲሞክራትዋ ተወዳዳሪ ሂለሪ ክሊንተን በበኩላቸው ፕረዚዳንቱ ከአሸባሪዎች ጋር ወግነዋል የሚለውን የትራምፕ አነጋገር አጥብቀው ነቅፈዋል።

“የፖለቲካ ክፍፍል በሚኖርበት ጊዜም እንኳን ቢሆን አንድ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንትነት የሚወዳደር ሰው ሊለው ከሚገባ አልፎ የሄደ አነጋገር ነው።”

ትራምፕ ባለፈው ሰኞ ባደረጉት ንግግር ፕረዚዳንት ከሆኑ የአሸባሪነት ታሪክ ካላቸው የአለም ክፍሎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ አግዳለሁ ብለዋል።

ፋይል- ዶናልድ ትራፕ
ፋይል- ዶናልድ ትራፕ

“የሂለሪ ክሊንተን ጎጂ የኢሚግረሽን እቅድ አክራሪ ሙስሊሞች በብዛት ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ በማድረግ በህብረተሰባችን ላይ ብቻ ሳይሆን በመላ የኑሮ ዘይባችን ላይ አደጋ ይጥላል።”

ፕረዚዳንት ኦባማ በግልጽ ነቀፌታ ውስጥ መግባታቸው ራሱ ዶናልድ ትራምፕ በሚያካሄዱት የምረጡኝ ዘመቻ ሁለት ዲሞክራት ተቃዋሚዎች ፕረዝዳንት ኦባማና ሂለሪ ክሊንተን ሳይገጥሟቸው አይቀርም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ዶናልድ ትራምፕ ሙስሊሞችን አስመልክቶ ያላቸውን አመለካከት አጥብቀው ነቀፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:54 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG