በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከአርጀንቲናው አቻቸው ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገሮች መካከል ስላለው ግንኙነት ተነጋግረዋል


ባለፈው ህዳር ሥልጣን የተረከቡት ፕሬዘዳንት ማክሪ ከዋሺንግተን ጋር ጠንካራ የኢኮኖሚ ትሥሥር ለመፍጠር እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በዛሬው እለት ከአርጀንቲናው አቻቸው ከማውሪስዮ ማክሪ (Mauricio Macri) ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገሮች መካከል ስላለው ግንኙነት ተነጋግረዋል።

ሚስተር ኦባማ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ብዌኖስ አይሬስ (Buenos Aires) አውሮፕላን ማረፊያ የደረሱት ትናንት ማለዳ ሲሆን፥ እለቱ በዚያች ሀገር ውስጥ ከ 40 ዓመታት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ከተደገፈው የመንግሥት ግልበጣ ቀን ጋር ተገጣጥሟል።

ትላንት በብራሰልስ የደረሰውን የሸብር ጥቃት ተከትሎ፥ በዋና ከተማዋ ብዌኖስ አይሬስ የፀጥታ ጥበቃው የተጠናከረ መሆኑ ተዘግቧል። በአንዳንድ ሥፍራ የባቡር አገልግሎቶች እንዲቋረጡ የተደረገ ሲሆን፥ ኦባማ በሚጎበኟቸው አካባቢዎች ያሉ መንገዶችም ታጥረዋል።

ባለፈው ህዳር ሥልጣን የተረከቡት ፕሬዘዳንት ማክሪ ከዋሺንግተን ጋር ጠንካራ የኢኮኖሚ ትሥሥር ለመፍጠር እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል። ዛሬ ምሽት ሁለቱ መሪዎች በእራት ግብዣ ወቅት ንግግር ካደረጉ በኋላ፣ ኦባማ እና ሚሼል የአርጀንቲናን ዳንስ ታንጉ እንዲደንሱ ተጋብዘዋል።

ኦባማና ሚሼል በአርጀንቲና የእራት ግብዣ ወቅት ታንጎ እንዲደንሱ ተጋብዘዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:40 0:00

XS
SM
MD
LG