በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ሀገሮችን የወከሉ ወጣት መሪዎችን ተቀበሉ


ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ሀገሮችን የወከሉ ወጣት መሪዎችን ተቀበሉ
ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ሀገሮችን የወከሉ ወጣት መሪዎችን ተቀበሉ

ከአሜሪካውያን አቻዎቻቸው ጋር እየተወያዩ ራዕያቸውን እያካፈሉና ልምድም እየቀሰሙ ናቸው

“እንደምን ዋላችሁ ወደሁዋይት ሐውስ እንኩዋን መጣችሁ ! ወደዩናይትድ ስቴትስም እንኩዋን ደህና መጣችሁ ! በዓለም ዋንጫው ካሸነፈችን ከጋና የመጣችሁትንም ወዳጆቻችንንም ማለቴ ነው ግዴለም! ለትንሽ ነው! 2014 ላይ እንገናኝ!” ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ

በዚህ መልክ ነበር ፕሬኢዘንት ባራክ ኦባማ ወደ መቶ ሃያ የሚደርሱት እና በየሀገሮቻቸው የባህል ልብሶች ደምቀው በማራሹ ዙሪያ ተቀምጠው የጠበቋቸውን ወንዶችና ሴቶች የአህጉረ አፍሪካ ወጣት መሪዎች የተቀበሏቸው።

ፕሬዚደንት ኦባማ ለዚህ መወያያ መድረክ ወጣቶቹን የጋበዟችው ይህ የአውሮፓውያን ሁለት ሺህ አስር ዓመተ ምህረት አስራ ሰባት የአፍሪካ ሀገሮች ከቅኝ አገዛዝ ተላቀው ነጻነታችውን የተጎናጸፉበትን ሃምሳኛ ዓመት መታሰቢያ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ከወጣቶቹ ጋር እናንተስ የቀጣዮቹ ሃምሳ ዓመታት ራዕያችሁ ምንድነው? በሚለው ዙሪያ ለማወያየት ነው።

የሃይማኖታዊ ተቋማት ፥ የሲል ማህበረሰባት የልማት እንዲሁም የንግድ ስራዎች መሪነታችሁን አስመስክራችኋል። ታላቅ ተስፋም ይጠብቃችኋል ። አያሌ እሪካውያን ለብዙ ጊዜ ያከናወኑትን የምትወክሉ ናችሁ። በርግጥም አፍሪካ ብዙ ጊዜ ልብ የማይባልላትን ወደሃያ አንደኛው ምዕተ በምታደርገው ግስጋሴ ያላትን ተስፋ የምታሳዩ ናችሁ ብለዋቸዋል።

ስለዚህም አሉ ጠንካራ እና በራሱዋ የምትተማመን አፍሪካ ታስፈልገናለች። ዓለምን የናንተን አፍሪካ ዓቅም ትፈልጋለች ፥ ሸሪካችሁ ለመሆንም ብለዋል። ስለዚህም ዛሬ በመካከላችን ያን ሽርክና ለማጠናከር የሚሰሩ የአስተዳደሬ አባላትም አሉ። ደስ ብሎኛል።

ለዚህ ለዛሬው ስብሰባችን ካሁን የሚመረጥ ጊዜ አይኖርም ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚደንት በአፍሪካ ዙሪያ አስራ ሰባት ሀገሮች የቅኝ ገዥዎች ባንዲራ ወርዶ የራሳቸው የነጻነት ሰንደቅ ዓላማቸውን በማውለብለብ በደስታ የፈነደቁበት ሃምሳኛ ዓመት ታሪካዊ ክብረ በዓል በመሆኑ ነው ብለዋል።

ፕሬዚደንቱ አያይዘው ዛሬም ቢሆን በአህጉሪቱ ዜጎች በፈታኝ ህይወት ውስጥ እንደሚያልፉም አንክድም ። ለልጆቻችን የለት ጉርስ እና ስራ ለማግኘት ያለባቸው ውጣ ውረድ እናውቃለን ብለው አዘውትሮ በዓለም መድረኮች የሚንጸባረቀው የአፍሪካ ገጽታም ይህ መሆኑንን እንረዳለን ብለዋል።

በጋና እና ቦትስዋና ብልጽግና እየተመዘገ ነው ሲሉም ፕሬዚደንት ኦባማ ተናግረዋል። ደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫን በስኬት ማከናወኑዋም አሉ ፕሬዚደንት ኦባማ ምንም እንኩዋን ወደአሸናፊነት የዘለቁት አውሮፓውያን የእግር ኳስ ቡድኖች ይሁኑ እንጂ የዓለም ዋንጫው ባለድል ግን አፍሪካ መሆንዋ ሲወሳላት እንደቆየ አስታውሰዋል።

ወጣቶቹን መሪዎች የቀጣዮቹን ሃምሳ ዓመታት አፍሪካን የመገንባት ኃላፊነት የናንተ ነው ሲሉ ኣሳስበዋቸዋል ። አሜሪካ አብራችሁ ትቆማለች በማለትም ለአህጉራችሁ ግልጽነትንና ሙስናን ለማስወገድ እንዲሰሩ አሳስበዋቸዋል።

መጪዎቹ የአፍሪካ መሪዎች እንዲህ ያለውን ግልጽነት ከልባቸው በመከተል ሙስና አስወጋጅ ርምጃዎችን የሚወስዱ ናችው። እንደHIV AIDS ካሉ በሽታዎች ራሳቸውን የሚጠብቁ የዜጎቻችን ሁሉ በተለይም የሴቶችን መብት የሚያስከብሩ ናቸው በማለት ካስገነዘቡ በኋላ የወደፊት ዕጣ ፈንታችሁ በናንተው ስራ ላይ ነው ብለዋል።

ፕሬዘንት ኦባማ ከወጣት አፍሪካውያኑ መሪዎች በርካታ ጥያቄዎችን በመቀበል አስተናግደዋል ፥ HIV AIDS ወረርሺኝ ፥ የአፍሪካ ሀገሮች የተማሩ ዜጎች ከሀገር ተሙዋጦ መውጣትን ፥ የሴቶች መብትንና ሌሎችንም ጥያቄዎችን አንስተውባባቸዋል። ደካማ አፍሪካ እና ብርቱዋ አሜሪካ ዕውን በዕኩልነት ላይ የተመሰረተ ሽርክና ሊኖራቸው ይችላል የሚል ጥያቄም ቀርቦላቸዋል።

አፍሪካውያኑ ወጣት መሪዎች ዛሬም በተሰናዱላቸው ልምድ መቅሰሚያ ራዕይ መጋሪያና ትውውቅ መፍጠሪያ ፕሮግራሞች መካፈላችውን ቀጥለዋል።

ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ፥ በአሜሪካ የሰላም ጉዋድ እና በተለያዩ ህዝባዊ ድርጅቶች መርሃ ግብሮች የነበሩዋቸው ሲሆን ነገ ሐሙስም ይቀጥላሉ።

XS
SM
MD
LG