በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦክላንድ ግልፅ ደብዳቤ ለፕሬዚዳንት ኦባማ


 አኑራድሃ ሚታል፤ ዋና ዳይሬክተር፤ ኦክላንድ ኢንስቲትዩት
አኑራድሃ ሚታል፤ ዋና ዳይሬክተር፤ ኦክላንድ ኢንስቲትዩት

በኢትዮጵያ ግዙፉ የውጭ የመሬት ኢንቨስትመንት እንዲቆም ኦባማ ተፅዕኖ እንዲያሣድሩ ተጠየቀ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ “በልማት ስም ይካሄዳል” ያለው የውጭ ባለሃብቶች መጠነ ሰፊ የመሬት ኢንቨስትመንት እንዲቆም ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላይ ጫና እንዲያሣድሩ የሚጠይቅ ግልፅ ደብዳቤ ኦክላንድ ኢንስቲትዩት አውጥቷል፡፡

ካሊፎርኒያ የሚገኘው ይህ ኢንስቲትዩት ግልፅ ደብዳቤውን ያወጣው ከትናንት በስተያ ግንቦት 11 ቀን 2004 ዓ.ም (በኢት የዘመን አቆጣጠር ነው) በሜሪላንዷ ካምፕ ዴቪድ ከተጠራው የስምንቱ ከበርቴ ሃገሮች - ጂ 8 ስብሰባ አንድ ቀን ቀደሞ ብሎ ነው፡፡

ደብዳቤው በወጣበት ዕለት በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ጉዳይ ላይ የተነጋገረ የስምንቱ ከበርቴ ሃገሮች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ሌሎች ሦስት የአፍሪካ መሪዎች የተገኙበት ሲምፖዚየም ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ተካሂዷል፡፡

“ውድ ፕሬዚዳንት ኦባማ፤

በምግብ ዋስትና ጉዳይ ላይ ለመምከር የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ ከአፍሪካ መሪዎች ጋር ግንቦት 11 ቀን በካምፕ ዴቪድ የሚያደርጉት ስብሰባ በአፍሪካ የምግብ ዋስትና እንዳይጨበጥ የሚያደርገውን፤ ምናልባት ብቸኛው ግዙፍ ሰው ሠራሽ አስተዋፅዖ አበርካች የሆነውን መጠነ-ሠፊውን በውጭ ባለሃብቶች የሚካሄድ የመሬት መዋዕለ-ነዋይን ጉዳይ ለመፈተሽ የሚያስችል ትልቅ አጋጣሚ ነው፡፡” ብሎ ይጀምራል በካሊፎርኒያው ኦክላንድ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አኑራድሃ ሚታል እና በ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሴ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ የተፈረመው ግልፅ ደብዳቤ፡፡

ይህ ስምንት ሺህ ደጋፊዎቻቸው እንደፈረሙት የሚናገረው ግልፅ ደብዳቤ ከጋምቤላ ሰባ ሺህ ሰው በግዳጅ እየተፈናቀለ መሆኑንና 150 ሺህ ተጨማሪ ሰው ወደ ሌላ ሥፍራ ለመውሰድ መታሰቡን፤ እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎች እንደሚካሄዱ ያመለክታል፡፡

የአሁኑን ግልፅ ደብዳቤ ካለፈው የካቲት ጀምሮ ሲያስፈርሙ እንደነበር የጠቆሙት ሚታል ከትልልቆቹ የኢትዮጵያ ለጋሾች ዩናይትድ ስቴትስ አንዷ እንደመሆኗ መጠን ጠንካራ መልዕክት ልናስተላልፍላቸው ሞክረናል ብለዋል የኦክላንድ ዋና ዳይሬክተር፡፡

አኑሪድሃ ሚታል ለቪኦኤ በሰጡት ቃለምልልስ ላይ የተዘጋጀውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG