በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒው ዮርክ ከተማ የባቡር ጣቢያ በደረሰ ጥቃት በርካታ ሰዎች ቆሰሉ


በኒው ዮርክ ከተማ የባቡር ጣቢያ በደረሰ ጥቃት በርካታ ሰዎች ቆሰሉ
በኒው ዮርክ ከተማ የባቡር ጣቢያ በደረሰ ጥቃት በርካታ ሰዎች ቆሰሉ

ብሩክሊን ሰንሴት ፓርክ በሚባለው የከተማዋ ቀበሌ የሠላሳ ስድስተኛው መንገድ የምድር ለምድር ባቡር ጣቢያ ውስጥ ጥቃቱ የደረሰው ጠዋት እንቅስቃሴ በሚበዛበት ሰዓት ላይ መሆኑን የከተማዋ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

ሰንሴት ፓርክ በሚባለው የሰራተኛ ሰፈር በሚገኘው የባቡር ጣቢያ በደረስው ጥቃት አስራ ስድስት ሰዎች የተጎዱ ሲሆን አስሩ በጥይት ተመትተው የቆሰሉ መሆናቸው ታውቋል። ከመካከላቸው አምስቱ በከባዱ የተጎዱ መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቁዋል።

ጥቃቱን ያደረሰው አደገኛ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አልዋለም ያሉት የኒው ዮርክ አገረ ገዢ ካቲ ሆከል ሰው በጣም እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።

የኒው ዮርክ ፖሊስ ኮሚሽነር በበኩላቸው ቀደም ብለው የወጡ ሪፖርቶች አጥቂው ፈንጂም ሳይጠቀም አልቀረም ብለው እንደነበር አውስተው አሁን ግን "በባቡር ጣቢያዎቻችን የተገኘ ፈንጂ የለም" ብለዋል።

አክለውም ታጣቂው ጥቃቱን በምን ምክንያት እንደፈጸመ ለጊዜው ግልጽ አይደለም ሆኖም ባሁኑ ወቅት ድንገቱን እየተከታተልን ያለነው እንደ የሽብር አድራጎት አይደለም ብለዋል።

የፖሊስ ኮምሽነሩ ሴዌል በሰጡት ቃል የግንባታ ሰራተኞች የሚለብሱትን የሚመስል አረንጓዴ ሰደሪያ የለበሰው ተጠርጣሪው አጭር ሰውነቱ ወፈር ያለ ጥቁር ወንድ መሆኑን ጠቁመዋል።

ተጠርጣሪ አጥቂው የጋዝ መከላከያ ፊቱ ላይ አጥልቆ ሲያበቃ ከቦርሳው ውስጥ የጢስ ጋዝ መያዣ አውጥቶ ከፍቶ ጢሱን ባቡሩ ውስጥ እንደለቀቀው ገልጸዋል።

በማስከተልም ባቡሩ ውስጥ እና መሳፈሪያው ላይ ያሉ ሰዎች ላይ እያነጣጠረ ጥይት መተኮሱን የፖሊስ ባለሥልጣኑ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG