በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ “የሽብር ሙከራ ነው” የተባለ ፍንዳታ ደረሰ


ኒው ዮርክ ከተማ
ኒው ዮርክ ከተማ

ዛሬ ሰኞ ዩናይትድ ስቴትስ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ አንድ አጥቂ ፖርት ኦቶሪቲ የአውቶብስ ጣቢያ አጠገብ ደረቱ ላይ የጠመጠመውን ቦምብ አፈንድቶ ራሱን እና ሌሎች ሦስት ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ።

ዛሬ ሰኞ ዩናይትድ ስቴትስ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ አንድ አጥቂ ፖርት ኦቶሪቲ የአውቶብስ ጣቢያ አጠገብ ደረቱ ላይ የጠመጠመውን ቦምብ አፈንድቶ ራሱን እና ሌሎች ሦስት ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ።

የኒው ዮርክ ከንቲባ ቢል ደ ብላሲዮ ድርጊቱን “የሽብር ጥቃት ሙከራ” ሲሉ ገልፀውታል።

ተጠርጣሪው አጥቂ አካዬድ ኡላህ የሚባል የሃያ ሰባት ዓመት ሰው መሆኑን የገለጹት የኒው ዮርክ ፖሊስ ኮሚሽነር ጄምስ ኦኒል በአሁኑ ጊዜ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ በአቅራቢያው በሚገኝ ሆስፒታል እየታከመ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኮሚሽነሩ ከንቲባ ደ ብላሲዮ እና ከኒው ዮርክ አገረ ገዢ አንድሩ ኮሞ ጎን ሆነው ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ቤት ውስጥ የተሰራ ፈንጂ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ “የሽብር ሙከራ ነው” የተባለ ፍንዳታ ደረሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:06 0:00

ከአጥቂው ሌላ ሦስት ሰዎች ለህይወት በማያሰጋ ሁኔታ መቁሰላቸውን የከተማዋ የእሳት አደጋ መከላከያ ባለሥልጣናት አመልክተዋል።

ከፍንዳታው በኋላ የከተማዋ አርባ ሁለተኛውና ሥምንተኛው ጎዳና አካባቢ ታጥረዋል። ብዛት ያላቸው የእሳት አደጋ መኪናዎችም ተሰማርተዋል። ከጥቃቱ ተከትሎ የከተማዋ የባቡር እገልግሎት መሥመሮች በከፍተኛ ደረጃ በመዘግየታቸውና በመሰረዛቸው ማንሃታን ውስጥ ያሉ በርካታ መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞቻቸውን ወደሥራ እንዳይሄዱ አድርገዋል። ጠዋቱን ተጓዦች እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን ማንሃታን ታይምስ ስኩዊር መሃል የሚገኘው የአርባ ሁለተኛው ጎዳና ጣቢያም ላይ ሳይቆሙ እያለፉት ሄደዋል።

እስከ ማምሻው የሰራተኛ መመለሻ ሰዓት ባለው ጊዜ የባቡር አገልግሎቶቹ ወደወትሮ መርኃ ግብሮቻቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ስለሁኔታው ገለፃ የተደረገላቸው መሆኑን የዋይት ሃውስ ቃል ኣቀባይ ሳራ ሃከቢ ሳንደርስ አመልክተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የእገር ደህንነት ሚኒስቴር ስለጥቃቱ በተያዘው ምርመራ ከፌዴራል የክፍለ ሀገርና የከተማ ባለልስጣናት እና ከአካባቢው ማህበረሰቦች ጋር በቅርበት ሆነን እየሰራን ነን ሲል አስታውቁዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG