በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ወጣቶች ቁጥር መጨመሩን ተገለፀ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ባለፉት 5ወራት በኮሮናቫይረስ የተያዙ ወጣቶች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።

የዚህ ምክንያቱ ለአካላዊ ርቀት ብዙም ትኩረት አለመሰጠቱ እንደሆነ አመልክተዋል። እኤአ ካለፈው የካቲት መጨረሻ እስከ ሃምሌ ወር አጋማሽ በነበረው ጊዜ ከተመዘገቡት 6ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ውስጥ 15ከመቶው በ15እና በ24 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል። በንፅፅር ከዚያ በፊት የነበረው የወጣቶቹ አሃዝ አራት ነጥብ አምስት ከመቶ እንደነበር ጠቅሷል።

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስቀድመንም ተናግረናል፣ አሁንም ደጋግመን እንናገራለን፤ ወጣቶች በኮሮናቫይረስ የማይደፈሩ አይደሉም ሊያዙ ሊታመሙ ህይወታቸው ሊያልፍ ሌሎችንም ሊያሲዙ ይችላሉ ሲሉ አሳስበዋል።

ከተቀሩት የህዝብ ክፍሎች ጋር ሲነፃፃር ወጣቶች የአካላዊ ርቀት መመሪያዎችን ችላ እንደሚሉ የጤና ጠበብት ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG