በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮርያ በደቡብ ኮርያ የሚካሄደው የክረምት ኦሊምፒክ ውድድር ልዑካን ለመላክ ተስማምታለች


ሰሜን ኮርያ በመጪው ወር በደቡብ ኮርያ ፕዮንግያንግ ወደሚካሄደው የክረምት ኦሊምፒክ ውድድር የከፍተኛ ደረጃ ልዑካን ለመላክ ተስማምታለች።

ሰሜን ኮርያ በመጪው ወር በደቡብ ኮርያ ፕዮንግያንግ ወደሚካሄደው የክረምት ኦሊምፒክ ውድድር የከፍተኛ ደረጃ ልዑካን ለመላክ ተስማምታለች።
ይህ ስምምነት የተደረገው ዛሬ ሰሜንና ደቡብ ኮርያ ተገናኝተው በተነጋገሩበት ወቅት ነው። ንግግሩ የተካሄደው “የሰላም መንደር” በተባለው ጳንሙንጆም ላይ ነው። በኮርያ ልሳነ ምድር ይካሄድ የነበርውን ጦርነት ያቆመው ስምምነት እኤአ በ1953 ዓ.ም የተፈረመው በዚሁ ቦታ ላይ ነበር።
ከፕዮንግያንግጉ ስብሰባ በኋላ ሰሜን ኮርያ የከፍተኛ ባለሥልጣኖች ልዑካንን፣ አትሌቶችንና ውድድሩን የሚያዳምቅ ቡድንን በመጪው ወር ወደ ሚጀመረው የኦሎምፒክ ውድድር የመላክ ዕቅድ እንዳላት የውኅደት ምክትል ሚኒስትር ገልጸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG