ከፍተኛ የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ስጋት መኖሩ፣ በሰሜንና በደቡብ ኮሪያዎች ዘንድ እየተሰማ መሆኑ ተነገረ።
ስጋቱ አሳሳቢ የሆነውም፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ጎብኚዎች ለ2018ቱ የክረምት ኦሊምፒክስ ውድድር፣ በደቡብ ኮሪያዋ ‘PyeongCang’ ሊገናኙ ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ መሆኑ እንደሆነም ታውቋል።
የሰሜን ኮሪያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳረጋገጠው፣ እአአ ካለፈው ታህሣሥ 1/2017 እስካሁኑ ጥር 16/ 2018 ድረስ፣ 8መቶ ሰዎች በዚሁ ተላላፊ መሆኑ በተነገረለት ተስቦ ተይዘዋል። ይህንኑ የሰሜን ኮሪያ መግለጫ፣ ዓለማቀፉ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማኅበር በመጽሔቱ አስፍሮት ለንባብ በቅቷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ