የሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የአንዳንድ ቀበሌዎች ነዋሪዎች በታጣቂዎች የሚደርሰውን ጥቃት በመሸሽ ቀዬአቸውንና ንብረታቸውን ጥለው እየሸሹ መኾናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ ከፍያለው አዳሬ ደግሞ፣ በደራ ወረዳም ኾነ በአጎራባች ወረዳዎች ለቀጠለው ጥቃት፣ የፋኖ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርገዋል።
የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች፣ ከሁለቱም ታጣቂ ቡድኖች ጋራ ውጊያ እያካሔዱ መኾኑንም፣ የዞኑ አስተዳዳሪ ገልጸዋል።
መድረክ / ፎረም