ዋሺንግተን ዲሲ —
የሰሜን ኮርያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪ ዮንግ ሆ ወደ ስዊድን አምርተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ተገናኝተው እንዲነጋገሩ ለማመቻቸት የታቀደ ተልዕኮ መሆኑ ተገልጿል።
ሪ ለሁለት ቀናት ጉብኘ ዛሬ ስቶክሆልም ገበተው ከስዊድኑ አቻቸው ማርጎት ዋልስትሮም ጋር ይነጋገራሉ። ስዊድን ሰሜን ኮርያ ባለው ኤምባሲው በኩል የዩናይትድ ስቴትስን፣ የካናዳንና የአውስትራልያን ዲፕሎማስያዊ ሥራን ይወክላል።
የስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ ሪ ጉብኝት ዓላማ የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ፕዮንይናግን በማውገዝ ያሳልፈው ውሳኔ በሚገባ እንዲተገበር በሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ ለማበርከት ነው ብሏል። ፕዮንግያንግ የተወገዘችው በኑክሌር መሳርያና በቦልስቲክ ሚሳይል ፕሮግራምዋ ምክንያት መሆኑ የሚታወቅ ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ