በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ሰብዓዊ መብት ባለሥልጣናት ለሰሜን ኮሪያ 60 ሚሊየን ክትባት እንዲላክ ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቁን ከመከፈታቸው በፊት በፀረ-ተባይ መደሃኒት ሲያጸዱ ፒዮንግያንግ፣ ሰሜን ኮሪያ፤ እአአ ዴሴምበር 28/ 2020
ፎቶ ፋይል፦ የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቁን ከመከፈታቸው በፊት በፀረ-ተባይ መደሃኒት ሲያጸዱ ፒዮንግያንግ፣ ሰሜን ኮሪያ፤ እአአ ዴሴምበር 28/ 2020

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሜን ኮሪያን በተመለከተ ቁልፍ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወደ ሀገሪቱ 60 ሚሊየን ያህል ክትባቶችን እንዲልክ ጠየቁ። ሰሜን ኮሪያ የተስፋፋ የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ ካልጀመሩ ሁለት የዓለም ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

ሰሜን ኮሪያ ኮቫክስ የተሰኘውን ዓለም አቀፍ የክትባት ሥርጭት መርኃ ግብርን ጨምሮ ከተለያዩ ዓለም ተቋማት በኩል የክትባት ልግስና ጥያቄ ቢቀርብላትም ሳትቀበለው ቀርታለች። ሰሜን ኮሪያ ክትባቱ መካከል ግማሹን ከተቀበለች በኃላ ሌላኛውን ገሚስ ክትባት ለማግኘት የጫና ሰለባ እሆናለሁ የሚል ሥጋት እንዳላት ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት መስማታቸውን ቶማስ ኦጄ ኪዊንታና የተባሉት የተባበሩት መንግሥታት ልዩ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሹም ተናግረዋል፤ በደቡብ ኮሪያ ሴዎል በነበረ የፕሬስ ማስገንዘቢያ ላይ።

የሰሜን ኮሪያን ህዝብ ሁለት ጊዜ ለመከተብ 60 ሚሊየን ክትባት እንደሚበቃ የጠቆሙት ኪዊንታና፣ ይሄ ዕቅድ በበሀገሪቱ ባለሥልጣናት በኩል ባይቀርብም፣ እሳቸው ግን የአውሮፓ ኅብረት ህብረትን ጨምሮ ለዲፕሎማቶች ሀሳቡን ማንሳታቸውን አስታውቀዋል።

በተመድ የህጻን መርጃ ድርጅት የክትባት ገበያ መዝገብ መሰረት በአሁኑ ጊዜ ኮቫክስ ለሰሜን ኮሪያ የመደበው ክተባት መጠን 1.29 ሚሊየን ብቻ ነው። መርኃ ግብሩ አስቀድሞ 8.1 ሚሊየን ገደማ ክትባት ለሰሜን ኮሪያ ቢመድብም ከሀገሪቱ መልስ በማጣቱ ቁጥሩን ቀንሷል።

ኮቫክስ የመደበውን አስትራዘኒካ ክትባት ፍቱንነት እና ደህነንነት ሰሜን ኮሪያ እንደሚያሳሰባት፣ የክትባቱን መጓጓዝ ሥራ የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ሰራተኞችን ወደ ግዛቷ ለማስገባት ሀገሪቱ ዳተኛ እንደሆነች ቪኦኤ በቀደቡ ዘገባዎች አውስቷል።

XS
SM
MD
LG