በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ ባለአጭር ርቀት ተወንጫፊ ሚሳይል ተኮሰች


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የጂ ሰባት የምጣኔ ሃብት ጉባዔ ላይ የተገኙ የዓለም መሪዎች የኒውክሊየር መሣሪያ ባለቤትነትን ምኞትዋን እንድትተው ከጥቂት ቀናት በፊት ያሳሰቡዋት ሰሜን ኮሪያ ዛሬም ባለአጭር ርቀት ተወንጫፊ ሚሳይል ለሙከራ ተኮሰች።

የጂ ሰባት የምጣኔ ሃብት ጉባዔ ላይ የተገኙ የዓለም መሪዎች የኒውክሊየር መሣሪያ ባለቤትነትን ምኞትዋን እንድትተው ከጥቂት ቀናት በፊት ያሳሰቡዋት ሰሜን ኮሪያ ዛሬም ባለአጭር ርቀት ተወንጫፊ ሚሳይል ለሙከራ ተኮሰች።

የዩናይትድ ስቴትስ የፓሲፊክ ዕዝ እንዳስታወቀው ከሰሜን ኮሪያ ምሥራቅ ጠረፍ የተተኮሰውን ሚሳይል ዕዙ የጃፓን የኢኮኖሚ ክልል ተብሎ የሚታወቀው ጃፓን ባሕር ከመጥለቁ ሥድስት ደቂቃ ቀደም ብሎ ተከታትሎታል።

ሚሳይሉ በሰሜን አሜርካ ላይ ምንም አደጋ እንዳልደቀነ የፓሲፊክ ዕዙ ገልፀል። የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ግን አጸፋ እንመልሳለን በማለት በቁጣ ዝተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ሰሜን ኮሪያ እንደገና ሚሳይል በመተኮስ ለአጎራባችዋ ቻይና ከባድ ንቀት አሳይታለች፡፡ ቻይና ግን የፒዮንግያንግ ወታደራዊ ምኞቶች ለመግታት ብርቱ ጥረት እያደረገች ነው ሲሉ በትዊተር አመስግነዋል።

የፕሬዚደንት ትራምፕ አስተዳደር እስካሁን ለሰሜን ኮሪያና ለመሪዋ ኪም ጆንግ ኡን በቃል ከባድ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ባለፈ ለዚያች ሃገር አድራጎት ምላሽ የሚሰጥበት ጠንካራ ፖሊሲ አላወጣም።

ይሁን እንጂ ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለውን ሁኔታ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍታት ካልተቻለ እና ወደ ጦርነት ከተገባ ከባድ መቅሰፍት ይከተላል ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG