በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኮሪያው መሪ በሩሲያ ጉብኝት ላይ ናቸው

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋራ ለመነጋገር፣ ዛሬ ማክሰኞ በባቡር ሩሲያ ገብተዋል።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋራ ለመነጋገር፣ ዛሬ ማክሰኞ በባቡር ሩሲያ ገብተዋል።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋራ ለመነጋገር፣ ዛሬ ማክሰኞ በባቡር ሩሲያ ገብተዋል።

አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በበኩላቸው፣ በሁለቱ መሪዎች መካከል የመሣሪያ ልውውጥ ስምምነት ሊኖር እንደሚችል በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።

“የመከላከያ ሚኒስቴራችን ኪም ጆንግ ኡን፣ በግል ባቡር ሩሲያ ሳይገቡ እንዳልቀረ ያምናል። በርካታ ወታደራዊ አጀብ እንደነበርም ታይቷል፤” ሲሉ፣ የደቡብ ኮሪያው የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

“የመሣሪያ እና የቴክኖሎጂ ዝውውርን አስመልክቶ ድርድር ይኖር እንደኹ በአንክሮ እየተከታተልን ነው፤” ሲሉ አክለዋል ቃል አቀባዩ።

ኪም እና ፑቲን፣ ሩሲያ በዩክሬን ለምታካሒደው ጦርነት የሚውል ተጨማሪ መሣሪያ ሰሜን ኮሪያ ስለምታቀርብበትና በምትኩም ሰሜን ኮሪያ ለሳተላይት እና ኑክሌር ለሚታጠቁ የውኃ ሰርጓጅ መርከቦቿ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን፣ እንዲሁም የምግብ ርዳታን ከሩሲያ ልታገኝ ስለምትችልበት ኹኔታ ሊነጋገሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ሰሜን ኮሪያ፣ በዩክሬን ጦርነት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መሣሪያ ለሩሲያ እንዳታስተላልፍ፣ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ እያስጠነቀቋት ይገኛሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG