በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ጦርነት ለሩሲያ ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች


የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም በአሙር
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም በአሙር

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ የሩሲያን ፕሬዚዳንት “ሙሉ በሙሉ እና ያለቅድመ ኹኔታ” እንደሚደግፉ አስታወቁ።

በምሥራቅ ሩሲያ የተገናኙት ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ስብሰባ፣ ሞስኮብ ዩክሬን ላይ ለከፈተችው ጦርነት መሣርያ የምታገኝበት መድረክ ሊኾን ይችላል፤ ስትል አሜሪካ በማስጠንቀቅ ላይ ናት፡፡

በምሥራቅ ሩሲያ በሚገኝ የመንኮራኩር ጣቢያ ውስጥ መሪዎቹ ለአራት ሰዓታት ባደረጉት ስብሰባ፣ የሁለቱ ሀገራት ፍላጎቶች አንድነት እንደተንጸባረቀበት ተመልክቷል።

ፑቲን፣ ድኻ ብትኾንም የሮኬት እና የጦር መሣሪያ ከፍተኛ ክምችት ካላት ሰሜን ኮሪያ የሚፈልጉት አለ።

ከኀምሳ ዓመታት በፊት በነበረው የኮሪያው ጦርነት፤ ሞስኮብ፣ ደቡብ ኮሪያን ለወረረችው ሰሜን ኮሪያ መሣሪያ ለግሳ ነበር። አሁን ደግሞ፣ ሰጪ እና ተቀባዩ ቦታ እንደተቀያየሩ ተዘግቧል።

በምትኩ ኪም ጁንግ ኡን፣ የወታደራዊ ሳተላይትን በማበልጸግ ረገድ የሩሲያን ርዳታ ይሻሉ። ይህም፣ በተደጋጋሚ ለከሸፈባቸውና ወታደራዊ ሳተላይትን ወደ ህዋ ለማምጠቅ የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያግዝ ነው፤ ተብሏል።

“ሩሲያ፣ ፍትሐዊ ጦርነት እያካሔደች ናት፤” ያሉት ኪም ጆንግ ኡን፣ ሰሜን ኮሪያ፥ የሩሲያ መንግሥት፣ “በጦርነቱ የሚወስዳቸውን ማንኛውንም ርምጃዎች፣ ሙሉ በሙሉ እና ያለቅድመ ኹኔታ ትደግፋለች፤” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG