በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ኮሪያ የጦር ኃይል ባለሥልጣናት ሹም ሽር

ባለፈው ሳምንት በገዢው ፓርቲ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ በተካሄደው ሹም ሽር በጦር ኃይሉ ሁለተኛው ከፍተኛ ባለሥልጣን መሪ ዮንግ ጊል ምትክ ፓክ ጆንግ ቾንግ እንደተሾሙ ይፋ ተደርጓል።

ሰሜን ኮሪያ በጦር ሠራዊቷ የሥልጣን እርከን ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን ባለሥልጣን በሌላ መተካቷን የመንግሥቱ የዜና ማሰራጫ ገለጠ።

ባለፈው ሳምንት በገዢው ፓርቲ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ በተካሄደው ሹም ሽር በጦር ኃይሉ ሁለተኛው ከፍተኛ ባለሥልጣን መሪ ዮንግ ጊል ምትክ ፓክ ጆንግ ቾንግ እንደተሾሙ ይፋ ተደርጓል።

የሹም ሽሩ ምክንያት አልተገለጸም። ይሁን እንጂ ፒዮንግያንግ እርምጃውን የወሰደችው ዩናይትድ ስቴትስ የጠላት ተግባር እየፈጸመችብን ነው በማለት የሚወነጅሉት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በአጸፋው፣ "የኒውክሊየር ክምችታችንን ማጎልበት እና በይበልጥ ኃይለኛ የሆኑ አህጉር ተሻጋሪ ሚሳይሎች መስራት አለብን" በሚሉበት ባሁኑ ወቅት መሆኑ ተጠቅሷል።

XS
SM
MD
LG