በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ ወደ ዲፕሎማሲ እንድትመለስ አሜሪካ ጠየቀች


ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ ኮሪያ ወታደሮች፣ ሰሜን ኮሪያ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ፓጁ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርጉ እአአ ጥር/24/2024.
ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ ኮሪያ ወታደሮች፣ ሰሜን ኮሪያ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ፓጁ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርጉ እአአ ጥር/24/2024.

ሰሜን ኮሪያ በመዲናዋ ፒዮንግያንግ የሚገኝንና ከደቡብ ኮሪያ ጋር በሰላም መልሶ ለመዋሃድ ያላትን ፍላጎት የሚያሳየውን ቅስት ማፍረሷን ተከትሎ፣ አገሪቱ ወደ ዲፕሎማሲ እንድትመለስ አሜሪካ በመጠየቅ ላይ ነች፡፡

ለአሥርት ዓመታት የቆየውን ቅስት በማፍረስ፣ ኪም ጆንግ ኡን ከደቡብ ኮሪያ ጋር በሰላም የመዋሃዱን ተስፋ አጨናግፈዋል ተብሏል።

ከአሜሪካ እና ከጎረቤቶቿ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ያለችው ሰሜን ኮሪያ፣ አዲስ ክሩዝ ሚሳዬል መሞከሯን ዛሬ ሐሙስ አስታውቃለች።

ደቡብ ኮሪያም የሰሜን ባላንጣዋ ወደ ምዕራባዊ የውሃ አካል አቅጣጫ ክሩዝ ሚሳዬል ማስወንጨፏን እነደደረሰችበት አረጋግጣለች፡፡

የሰሜን ኮሪያ የሚሳዬል እንቅስቃሴዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የታገዱ ባይሆኑም፣ ለደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ግን የስጋት ምንጭ ናቸው።

ሰሜን ኮሪያ በያዝነው ወር ብቻ ተደጋጋሚ የሚሳዬል ሙከራዎችን አድርጋለች፡፡ ሙከራዎቹ በጃፓን እና በጉዋም በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ሠፈሮች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG