በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳዬል ሞከረች


ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ሰኞ አህጉር አቋራጭ ሚሳዬል ለሙከራ ወደ ባሕር መተኮሷን ደቡብ ኮሪያ አስታውቃለች፡፡
ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ሰኞ አህጉር አቋራጭ ሚሳዬል ለሙከራ ወደ ባሕር መተኮሷን ደቡብ ኮሪያ አስታውቃለች፡፡

ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ሰኞ አህጉር አቋራጭ ሚሳዬል ለሙከራ ወደ ባሕር መተኮሷን ደቡብ ኮሪያ አስታውቃለች፡፡ በአንድ ቀን ውስጥ ለሁለተኛ ግዜ የተተኮሰ ሚሳዬል ነው ተብሏል።

ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ ሚሳዬሉን ዛሬ ስትተኩስ፣ ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ መሆኑን እና፣ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የኑክሌር መከላከል አቅማቸውን ለማጠናከር በትብብር ለመወሰናቸው የተሰጠ መልስ እንደሆነ ተነግሯል።

አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በጋራ የሚያደርጉት ልምምድን ሰሜን ኮሪያ ግልጽ የሆነ ማስፈራሪያ አድርጋ እንደምትመለከተው የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለሙከራ የተተኮሰው ሚሳዬል፣ ሰሜን ኮሪያ ካሏት መሣሪያዎች እጅግ ኃይለኛው እንደሆነ ፕሬዝደንት ኪም ጆንግ ኡን ገልጸዋል።

ሚሳዬሉ 1ሺሕ ኪሜ ከተምዘገዘገ በኋላ፣ በሰሜን ኮሪያ እና በጃፓን መካከል ከሚገኘው የውሃ አካል ላይ ማረፉ ታውቋል። በጎረቤት አገራቱ እንዳይሰማም 6ሺሕ ኪሜ ከፍ ተደርጎ መተኮሱም ተመልክቷል።

ከደቡብ ኮሪያ እና ከጃፓን አቻዎቻቸው ጋር በስልክ የተነጋገሩት የአሜሪካው ብሔራዊ የፀጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቨን፣ የሰሜን ኮሪያ ሙከራ፣ አገሪቱ የባሊስቲክ ሚሳዬል ሙከራ እንዳታደርግ የተመድ የፀጥታው ም/ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ የጣሰ ነው ብልዋል።

የአሜሪካ እና ይደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ባለፈው ዓርብ ዋሽንግተን ላይ ተገናኝተው፣ በሚቀጥለው በጋ የሚያደርጉት ልምምድ የኑክሌር ጥቃትን መከላከል ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ተስማምተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG