በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ ከትናንት ወዲህ ብቻ 27 ሚሳዬሎችን አስወነጨፈች


የሰሜን ኮሪያን ሚሳኤል ሙከራ የሚያሳይ የዜና ስርጭት
የሰሜን ኮሪያን ሚሳኤል ሙከራ የሚያሳይ የዜና ስርጭት

ሰሜን ኮሪያ ትናንት 24 ተከታታይ ሚሳዬሎችን ካስወነጨፈች በኋላ ዛሬ ሦስት ደግማለች። ከነዚህም ውስጥ አንደኛው ረጅም ርቀት ተወንጫፊ በመሆኑ በጃፓን በሚገኙ ሦስት ግዛቶች አስቸኳይ የአደጋ ጥሪ ተደርጎ ሰዎች ባሉበት እንዲጠለሉ ተዕዛዝ ተላልፎ ነበር።

ሰሜን ኮሪያ ሚሳይሎቹን ያስወነጨፈችው አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ እያከናወኑት ባለው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ቁጣዋን ለመግለጽ ነው ተብሏል። የሚሳዬል ውንጨፋዎቹን ያጀቡ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ከባድ መሣሪያዎችንም ተኩሳለች።

በጃፓን አንዳንድ አካባቢዎች የቴሌቭዥን ስርጭቶች ተቋርጠው የአደጋ ማስጠንቀቂያ መልዕክቶች ተላልፈዋል። የማስጠንቀቂያዎቹ ስርጭቶች ሚሳዬሉ በጃፓን ግዛት በኩል እንዳለፈ ቢገልጹም፣ የሃገሪቱ የመከላከያ ባለሥልጣናት ግን ሚሳዬሉ በኮሪያ ባህረ-ገብ መሬትና በጃፓን መካከል ባለው ባህር ላይ ካለፈ በኋላ ወዴት እንደደረሰ እንዳላወቁ ተናግረዋል።

ደቡብ ኮሪያ በምላሹ የጦር አውሮፕላኖቿን አስነስታ ሶስት ሚሳዬሎችን ከባህር ድንበራቸው በስተሰሜን አቅጣጫ አስወንጭፋለች። ይህም ደቡብ ኮሪያ ጠላቶቿን አነጣጣራ ምምታት እንደምትችል ለማሳየት ነው ተብሏል።

እአአ ከ1950 እስከ 1953 ከተካሄደው የኮሪያ ጦርነት ወዲህ ሁለቱ ወገኖች ድንበር ተሻጋሪ ሚሳዬል አስወንጭፈው አያውቁም። ትናንት ሁለቱም ያስወነጨፉት ግን አንድ ሰዓት ርቀት ላይ የነበረ ነው ተብሏል።

ሰሜን ኮሪያ በዚህ ዓመት ከ50 በላይ ባሊስቲክ ሚስዬሎችን ብታስወነጭፍም፣ የትናንቱ ግን ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ደቡብ ኮሪያ አቅጣጫ የተወነጨፈ ሲሆን የአስቸኳይ ግዜ ማስጠንቀቂያ የታወጀበትን ሁኔታ ፈጥረዋል።

የአሜሪካ ብሔራዊ ጸጥታ ም/ቤት ባወጣው መግለጫ የአገር አቋራጭ ሚሳዬሎቹን መወንጨፍ በብርቱ ካወገዘ በኋላ፣ ዩናይትድ ስቴትስን፣ የደቡብ ኮሪያንንና የጃፓንን ደህንነት ለማረጋገጥ “አስፈላጊ እርምጃዎችን ሁሉ” እንወስዳለን ሲል ዝቷል። የውጪ ጕዳይ መሥሪያ ቤት በበኩሉ ድርጊቱ የተመድን የጸጥታ ም/ቤት ውሳኔ በግልጽ የጣሰ ነው ብሏል።

XS
SM
MD
LG