ሰሜን ኮሪያ አየር ላይ እንዳለ ፈንድቶ ስብርባሪው ዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ አቅራቢያ ስለተበተነው ሚሳይሏ ድምጿን እንዳጠፋች ነች።
የመንግሥቱ የዜና ማሰራጫዎች ትናንት ረቡዕ ሰለደረሰው አደጋ ምንም አልተናገሩም።
ሚሳይሉ ከትልቁ የሀገሪቱ አውሮፕላን ጣቢያ በተተኮሰ በጥቂት ጊዜ ውስጥ አየር ላይ መፈንዳቱን የደቡብ ኮሪያ የጦር ኃይል አስታውቋል። ሚሳይሉ የወደቀው ሰው የሚኖርበት አካባቢ ይሁን አይሁን አልተገለጸም።