በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳዬል ሙከራ አካሄደች


የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል ሙከራ የሚያሳይ ምስል
የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል ሙከራ የሚያሳይ ምስል

ሰሜን ኮሪያ እአአ ከ2017 ጀምሮ ክፍለ አህጉራትን አቋራጭ የሚመስል የባለስቲክ ሚሳዬል ሙከራ ማድረጓን የጃፓንና የደቡብ ኮሪያ መንግሥታት አስታወቁ፡፡

የጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ኮሪያ ሚሳዬሎች ከጃፓኑ አሞሪ 170 ከሚሎትር በስተ ምዕራብ በሚገኘው ልዩ የኤኮኖሚ ዞን ለማረፍ ለ70 ደቂቃዎች የሚጓዙ መሆኑን አስታውቋል፡፡

እንደ ጃፓን ባለሥልጣናት መግለጫ በዓይነቱ አዲስ የሆነ ICBM ዝርያ ያለው ሚሳዬሉ ሽቅብ ወደላይ 6ሺ ኪሜትር መውጣት የሚችል ሲሆን ወደ ጎን ደግሞ እስከ 1ሺ100 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችል ነው፡፡

የደቡብ ኮሪያ የደህንነት ምክር ቤት ባለሥልጣናት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጄ ኢን ሰሜን ኮሪያ የረጅም ሚሳዬሎችን አስመልክቶ ራሷ የገባቸውን ህግ ጥሳለች ሲሉ ሙከራውን በጽኑ ኮንነዋል፡፡

ይህ የአውሮፓውያኑ ዓመት ከገባ ወዲህ ሰሜን ኮሪያ እስካሁ 12 ዙር ሚሳዬሎች ለሙከራ መተኮሷን ሲገለጽ ከነዚህ ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ ከሳተላይት ለመተኮስ የሚያስችል ሙከራ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG