የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሳምንቱን መጨረሻ የመሣሪያ ማምረቻዎችን ሲጎበኙ እና አነጣጥሮ ተኳሽ ጠመንጃዎችን ሲተኩሱ እንዳሳለፉ መንግስታዊው የዜና ወኪል አስታውቋል።
ኪም በተጨማሪም በርካታ የሮኬት ተኳሽ ተሽከርካሪዎችን ሲነዱ የስተውለዋል።
በዜና ማሰራጫው ከተለቀቁ ምሥሎች ውስጥ ለኢላማ የተቀመጠው ምስል መሃሉ ተነጣጥሮ መመታቱን ሲያሳይ፣ ተኳሹ ኪም ጁንግ ኡን ይሁኑ ሌላ ግለሰብ የዜና ማሰራጫው ያለው የለም።
ኪም ዘመናዊ ተተኳሾችን የሚያመርተውን ፋብሪካም ጉብኝተዋል።
የውጪ ተንታኞች እንዳይጠቀሙበት በሚልም የተለቀቁት አንዳንድ ፎቶግራፎች አንዳንድ ቦታዎችን እና የባለሥልታናት ፊትን አደብዝዞ አሳይቷል።
ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ለምታካሂደው ጦርነት የሚውሉ መሣሪያዎችን ታቀብላለች ሲሉ አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ ክስ ያሰማሉ።
ከሰሜን ኮሪያ የሚላኩት ሚሳዬሎች በትክክል ኢላማቸውን እንደማይመቱ የዩክሬን ባለሥልጣናት በመናገር ላይ መሆናቸውን አንዳንድ የሚዲያ ዘገባዎች በማመልከት ላይ ናቸው።
መድረክ / ፎረም