የዩናይትድ ስቴትስ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ወደ ደቡብ ኮሪያ መምጣቷን ተከትሎ፣ ሰሜን ኮሪያ ሁለት የአጭር ርቀት ቦለስቲክ ሚሳኤሎችን ከምስራቃዊ ባህሯ ላይ ማስወንጨፏን የደቡብ ኮሪያ ጦር ሠራዊት ዛሬ አስታወቀ። ‘ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየጨመረ የመጣው የፒዮንግያንግ የጦር መሳሪያ ሙከራ የዩናይትድ ስቴትስ ግዙፍ የጦር መርከቦች ወደ ደቡብ ኮሪያ መምጣታቸውን በመቃወም ሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ኃይሏን ለማሳየት ያደረገችው ነው’ ሲል የደቡብ ኮሪያ ጦር ሠራዊት አክሎ አመልክቷል።
የደቡብ ኮሪያ ጠቅላይ ጦር አዛዥ ፤ “ሰሜን ኮሪያ ካለፈው ሳምንት አንስቶ በያዘችው ሦስተኛ ዙር የጦር መሳሪያ ሙከራዋ በአገሬው የሰዓት አቆጣጠር እኩለ ሌሊት ከማለፉ ጥቂት ቀደም ብሎ ነው፤ ከመዲናዋ ፒዮንግያንግ አቅራቢያ ካለ ሥፍራ ሚሳይሎቹን አስወንጭፋለች” ሲሉ አስረድተዋል።
ሁለቱም ሚሳኤሎች በኮሪያ ባሕረ ገብ መሬት ምሥራቃዊ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ካለ ውሃ ላይ ከማረፋቸው አስቀድሞ 400 ኪሎ ሜትሮች መምዘግዘጋቸውን ያመለከተው መግለጫ አክሎም፤ “የአካባቢውን ሰላም እና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል ከባድ ትንኮሳ ነው" ሲል ኮንኖታል።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳም በበኩላቸው፣ የሚሳይል ሙከራውን በተመለከተ መንግሥታቸው ቤጂንግ በሚገኘው ኤምባሲያቸው በኩል ለሰሜን ኮሪያ ተቃውሞውን ማሰማቱን ተናግረዋል። ቶኪዮ ከዋሽንግተን እና ከሶል ጋራ ካላት የሦስትዮሽ የፀጥታ ትብብርን ትይዩ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ላይ ነች ነው’ ብለዋል ።
ከሃገሪቱ ልዩ የኢኮኖሚ ክልል ወጣ ያለ ሥፍራ ላይ ያረፉት ሚሳኤሎች ያደረሱት ጉዳት አለመኖሩንም የጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር አመልክቷል።
መድረክ / ፎረም