በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ በጃፓን አናት ላይ ያለፈ የሚሳይል ሙከራ አካሂዳለች


ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ማለዳ በጃፓን አናት ላይ ያለፈ የሚሳይል ሙከራ አካሂዳለች።

ፒዮንግያንግ በቅርቡ በዩናይትድ ስቴትስ ግዛት በጉዓም አቅራቢያ ለመተኮስ አቅዳ ከሰረዘችው የሚሳይል ሙከራ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ። ያ የሰሜን ኮሪያ እቅድ ከጃፓንና ከሌሎች መሪዎች ብርቱ ነቀፋን እንዳስከተለባት ይታወቃል።

በካሊፎርኒያ የዓለምቀፍ ጥናት ማዕከል የሚሳይል ባለሞያው ጄፈሪ ልዊስ እንደሚሉት ይህ ከ3 እስከ 5ሺህ ኪሎ ሜትር ተጓዡ ሃዋሶን /Hwasong12/ የተባለው ቦለስቲክ ሚሳይል የዛሬው ሁለተኛው ሙከራዋ ሲሆን የተሳካለት ነው።

ፒዮንግያንግ ቀደም ሲል ባለፈው ግንቦት ያካሄደችው ሙከራ የመጀመሪያው ስኬታማ ጥረቷ ነው ተብሏል።

ሰሜን ኮሪያ ዛሬ የተኮሰችው ቦሊስቲክ ሚሳይል በጃፓን አየር ላይ በጣም ከፍ ብሎ ያለፈው ከተተኮሰ 10 ደቂቃ በኋላ ሲሆን ፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ ከማረፉ በፊት ሦስት ቦታዎች ላይ ተከፋፍሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG